1 ዜና መዋዕል 1:34 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አብርሃምም ይስሐቅን ወለደ። የይስሐቅም ልጆች ዔሳውና እስራኤል ነበሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አብርሃም ይሥሐቅን ወለደ። የይሥሐቅ ወንዶች ልጆች፤ ዔሳው፣ እስራኤል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የአብርሃም ልጅ ይስሐቅ፥ ዔሳውንና ያዕቆብን ወለደ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አብርሃምም ይስሐቅን ወለደ። የይስሐቅም ልጆች ዔሳውና ያዕቆብ ነበሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አብርሃምም ይስሐቅን ወለደ። የይስሐቅም ልጆች ዔሳውና እስራኤል ነበሩ። |
ሰውየውም፦ “ከእንግዲህ ወዲህ ስምህ ያዕቆብ አይባልም፤ ነገር ግን ከእግዚአብሔር ከሰውም ጋር ታግለህ አሸንፈሃልና እስራኤል ይባላል” አለው።
የመገረዝንም ኪዳን ሰጠው፤ እንዲሁም ይስሐቅን ወለደ፤ በስምንተኛውም ቀን ገረዘው፤ ይስሐቅም ያዕቆብን ያዕቆብም ዐሥራ ሁለቱን የአባቶችን አለቆች።