ዘኍል 10:9 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በሚገፋችሁም ጠላት ላይ በምድራችሁ ወደ ሰልፍ ስትወጡ ከፍ ባለ ድምፅ መለከቶቹን ንፉ፤ በእግዚአብሔርም በአምላካችሁ ፊት ትታሰባላችሁ፥ ከጠላቶቻችሁም ትድናላችሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በገዛ ምድራችሁ በግፍ በመጣባችሁ ጠላት ላይ ስትዘምቱ መለከቶቹን ከፍ ባለ ድምፅ ንፉ፤ በእግዚአብሔር በአምላካችሁ ትታሰባላችሁ፤ ከጠላታችሁም እጅ ትድናላችሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በሚቃወማችሁም ጠላት ላይ በምድራችሁ ወደ ጦርነት ስትወጡ ከፍ ባለ ድምፅ ማስጠንቀቂያውን በመለከቶቹ ንፉ፤ በጌታም በአምላካችሁ ፊት ትታወሳላችሁ፥ ከጠላቶቻችሁም ትድናላችሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “በአገራችሁ ላይ ጦርነት አንሥቶ አደጋ የጣለባችሁን ጠላት ለመከላከል ስትሄዱ በእኔ በአምላካችሁ በእግዚአብሔር ዘንድ እንድትታወሱ በመለከቶቻችሁ የማስጠንቀቂያ ድምፅ ንፉ፤ እኔ አምላካችሁም አድናችኋለሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በሚገፋችሁም ጠላት ላይ በምድራችሁ ወደ ሰልፍ ስትወጡ በምልክት መለከቶችን ንፉ፤ በእግዚአብሔርም በአምላካችሁ ፊት ትታሰባላችሁ፤ ከጠላቶቻችሁም ትድናላችሁ። |
እነሆም፥ እግዚአብሔር በእኛ ላይ አለቃ ነው፤ መለከቱንም የሚነፉ ካህናቱ ከእኛ ጋር ናቸው፤ በእናንተም ላይ ይጮኸሉ። የእስራኤ ልጆች ሆይ፥ አይበጃችሁምና ከአባቶቻሁ አምላክ ከእግዚአብሔር ጋር አትዋጉ።”
አንጀቴ! አንጀቴ! ልቤ በጣም ታምሞአል፥ በውስጤም ልቤ ታውኮብኛል፥ ነፍሴ ሆይ፥ የመለከትን ድምፅና የሰልፍን ውካታ ሰምተሻልና ዝም እል ዘንድ አልችልም።
በይሁዳ ዘንድ ተናገሩ በኢየሩሳሌምም ላይ አውሩና፦ በአገሪቱ ላይ መለከት ንፉ በሉ፥ ጮኻችሁም፦ ሁላችሁ ተሰብሰቡ ወደ ተመሸጉትም ከተሞች እንግባ በሉ።
ስለዚህ፥ እነሆ፥ በአሞን ልጆች ከተማ በረባት ላይ የሰልፍ ውካታን የማሰማበት ዘመን ይመጣል፥ ይላል እግዚአብሔር፥ የፍርስራሽ ክምርም ትሆናለች፥ ሴቶች ልጆችዋም በእሳት ይቃጠላሉ፥ እስራኤልም የወረሱትን ይወርሳል፥ ይላል እግዚአብሔር።
እናንተ የብንያም ልጆች፥ ክፉ ነገር ታላቅም ጥፋት ከሰሜን ይጐበኛልና ከኢየሩሳሌም ውስጥ ሽሹ፥ በቴቁሔ መለከቱን ንፉ፥ በቤትሐካሪም ላይ ምልክት አንሡ።
ለእስራኤል ልጆች እንዲህ ብለህ ንገራቸው፦ በሰባተኛው ወር በመጀመሪያው ቀን ዕረፍት፥ በመለከት ድምፅ መታሰቢያ፥ የተቀደሰ ጉባኤ ይሁንላችሁ።
ሙሴም ከየነገዱ አንድ አንድ ሺህ ወደ ጦርነት ሰደደ፤ እነርሱንና የካህኑን የአልዓዛርን ልጅ ፊንሐስን ወደ ጦርነት ሰደዳቸው፤ የመቅደሱንም ዕቃ የሚነፋውንም መለከት በእጁ ሰጠው።
ጠላቶችህን ለመውጋት በወጣህ ጊዜ፥ ፈረሶችንና ሰረገሎችን ሕዝቡንም ከአንተ ይልቅ በዝተው ባየህ ጊዜ፥ ከግብፅ አገር ያወጣህ አምላክህ እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ነውና አትፍራቸው።
ቀንደ መለከቱም ባለማቋረጥ ሲነፋ፥ የመለከቱን ድምፅ ስትሰሙ፥ ሕዝቡ ሁሉ ታላቅ ጩኸት ይጩኹ፥ የከተማይቱም ቅጥር ይወድቃል፥ ሕዝቡም ሁሉ እያንዳንዱ አቅንቶ ይገባባታል።
በዚያም ዓመት የእስራኤልን ልጆች ሥቃይ አበዙባቸው፥ በዮርዳኖስ ማዶ በአሞራውያን አገር በገለዓድ ውስጥ ያሉትን የእስራኤልን ልጆች ሁሉ አሥራ ስምንት ዓመት ተጋፉአቸው።
እግዚአብሔርም መሳፍንትን ባስነሣላቸው ጊዜ እግዚአብሔር ከመስፍኑ ጋር ነበረ፥ እግዚአብሔርም ስለሚጋፉአቸውና ስለሚያስጨንቋቸው በጩኸታቸው ያዝን ነበርና በመስፍኑ ዘመን ሁሉ ከጠላቶቻቸው እጅ አዳናቸው።
በመጣም ጊዜ በተራራማው በኤፍሬም አገር ቀንደ መለከት ነፋ፥ የእስራኤልም ልጆች ከእርሱ ጋር ከተራራማው አገር ወረዱ፥ እርሱም በፊታቸው ሄደ።
የእስራኤልንም ልጆች የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እስራኤልን ከግብጽ አወጣሁ፥ ከግብጻውያንም እጅ ከሚያስጨንቁአችሁም ነገሥታት ሁሉ እጅ አዳንኋችሁ።