Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘኍል 10:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 በሚቃወማችሁም ጠላት ላይ በምድራችሁ ወደ ጦርነት ስትወጡ ከፍ ባለ ድምፅ ማስጠንቀቂያውን በመለከቶቹ ንፉ፤ በጌታም በአምላካችሁ ፊት ትታወሳላችሁ፥ ከጠላቶቻችሁም ትድናላችሁ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 በገዛ ምድራችሁ በግፍ በመጣባችሁ ጠላት ላይ ስትዘምቱ መለከቶቹን ከፍ ባለ ድምፅ ንፉ፤ በእግዚአብሔር በአምላካችሁ ትታሰባላችሁ፤ ከጠላታችሁም እጅ ትድናላችሁ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 “በአገራችሁ ላይ ጦርነት አንሥቶ አደጋ የጣለባችሁን ጠላት ለመከላከል ስትሄዱ በእኔ በአምላካችሁ በእግዚአብሔር ዘንድ እንድትታወሱ በመለከቶቻችሁ የማስጠንቀቂያ ድምፅ ንፉ፤ እኔ አምላካችሁም አድናችኋለሁ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 በሚ​ገ​ፋ​ች​ሁም ጠላት ላይ በም​ድ​ራ​ችሁ ወደ ሰልፍ ስት​ወጡ በም​ል​ክት መለ​ከ​ቶ​ችን ንፉ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በአ​ም​ላ​ካ​ችሁ ፊት ትታ​ሰ​ባ​ላ​ችሁ፤ ከጠ​ላ​ቶ​ቻ​ች​ሁም ትድ​ና​ላ​ችሁ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 በሚገፋችሁም ጠላት ላይ በምድራችሁ ወደ ሰልፍ ስትወጡ ከፍ ባለ ድምፅ መለከቶቹን ንፉ፤ በእግዚአብሔርም በአምላካችሁ ፊት ትታሰባላችሁ፥ ከጠላቶቻችሁም ትድናላችሁ።

Ver Capítulo Copiar




ዘኍል 10:9
34 Referencias Cruzadas  

እንዲህ አላቸው፤ “የእስራኤል አምላክ ጌታ እንዲህ ይላል፤ ‘እስራኤልን ከግብጽ አወጣሁት፤ ከግብፃውያን እጅ ይጨቁኗችሁ ከነበሩት ከሌሎቹ መንግሥታት ሁሉ እጅ ታደግኋችሁ።’


ጌታ መሳፍንትን ባስነሣላቸው ጊዜ ከመስፍኑ ጋር ስለሚሆን፥ እርሱ በሕይወት እስካለ ድረስ ጌታ ከጠላቶቻቸው ያድናቸው ነበር፤ ከጠላቶቻቸው ሥቃይና መከራ ሲደርስባቸው በሚጮኹበት ጊዜ ጌታ ይራራላቸው ነበር።


እግዚአብሔር ኖኅንና ከእርሱ ጋር በመርከቡ ውስጥ የነበሩትን አራዊትና እንስሶች ሁሉ አሰበ። ነፋስ በምድር ላይ እንዲነፍስ አደረገ፥ ውኃውም ጎደለ፥


ጠላቶቻቸውም ግፍ አደረጉባቸው፥ ከእጃቸውም በታች ተዋረዱ።


አቤቱ፥ በሕዝብህ ሞገስ አስበኝ፥ በመድኃኒትህም ጐብኘኝ፥


ይሁዳም ወደ ኋላው በተመለከተ ጊዜ፥ እነሆ፥ ጦርነቱ በፊቱና በኋላው ነበረ፤ ወደ ጌታም ጮኹ፥ ካህናቱም መለከቱን ነፉ።


ሲዶናውያን፥ አማሌቃውያንና ማዖናውያን አሠቃዩአችሁ፤ እናንተም እንድረዳችሁ ወደ እኔ ጮኻችሁ፤ ታዲያ እኔ ከእጃቸው አላዳንኋችሁምን?


በዚያም ዓመት የእስራኤልን ልጆች ሥቃይ አበዙባቸው፥ በዮርዳኖስ ማዶ በአሞራውያን አገር በገለዓድ ውስጥ ያሉትን የእስራኤልን ልጆች ሁሉ ዐሥራ ስምንት ዓመት ተጋፉአቸው።


ቀንደ መለከቱም ባለማቋረጥ ሲነፋ፥ የመለከቱን ድምፅ ስትሰሙ፥ ሕዝቡ ሁሉ ታላቅ ጩኸት ይጩኹ፤ የከተማይቱም ቅጥር ይወድቃል፥ ሕዝቡም ሁሉ እያንዳንዱ ወደ እርሷ አቅንቶ በቀጥታ ይገባል።”


ሙሴም ከየነገዱ አንድ አንድ ሺህ ወደ ጦርነት ላከ፤ እነርሱንና የካህኑን የአልዓዛርን ልጅ ፊንሐስን ወደ ጦርነት ላካቸው፤ የመቅደሱንም ዕቃ የሚነፋውንም የማስጠንቀቂያ መለከት በእጁ ሰጠው።


ደግሞም መለከት ትክክል ያልሆነ የጥሪ ድምፅ ካሰማ፥ ለጦርነት ማን ይዘጋጃል?


ወይስ በከተማ ውስጥ መለከት ቢነፋ ሕዝቡ አይፈራምን? ወይስ ጌታ ካላደረገው በቀር በከተማ ላይ ክፉ ነገር ይሆናልን?


እኔም፦ ‘የመለከቱን ድምፅ አድምጡ’ ብዬ ጠባቆችን ሾምሁባችሁ፤ እነርሱ ግን፦ ‘አናደምጥም’ አሉ።


ዓላማውን የምመለከት፥ የመለከቱንስ ድምፅ የምሰማ እስከ መቼ ነው?


አንጀቴ! አንጀቴ! ልቤ በጣም ታምሞአል፥ በውስጤም ልቤ ታውኮብኛል፤ ነፍሴ ሆይ! የመለከትን ድምፅና የጦርነትን ሁካታ ሰምተሻልና ዝም ማለት አልችልም።


በይሁዳ ላይ ተናገሩ በኢየሩሳሌምም ላይ አውጁ፦ “በአገሪቱ ላይ መለከት ንፉ በሉ፤ ጮኻችሁም፦ ‘ሁላችሁ ተሰብሰቡ ወደ ተመሸጉትም ከተሞች እንግባ’ በሉ።


በኃይልህ ጩኽ፥ አትቈጥብ፥ ድምፅህን እንደ መለከት አንሣ፥ ለሕዝቤ መተላለፋቸውን ለያዕቆብ ቤትም ኃጢአታቸውን ንገር።


እናንት በዓለም ውስጥ ያላችሁና በምድር የምትኖሩ ሕዝቦች ሆይ፥ ምልክት በተራሮች ላይ በሚወጣ ጊዜ ተመልከቱ! መለከትም በተነፋ ጊዜ ስሙ!


እኛን በመዋረዳችን አስቦናልና፥ ፍቅሩ ለዘለዓለም ነውና፥


ከዚያም የጌታ መንፈስ በጌዴዎን ላይ ወረደ፤ እርሱም መለከት ነፋ፤ አቢዔዝራውያን እንዲከተሉት ጠራቸው።


ከግብፃውያን እጅ ታደግኋችሁ፤ ከሚያስጨንቋችሁ ሁሉ አዳንኋችሁ፤ እነርሱንም ከፊታችሁ አሳድጄ አስወጣኋቸው፤ ምድራቸውንም ሰጠኋችሁ።”


እዚያም እንደ ደረሰ፥ በኰረብታማው በኤፍሬም ምድር ቀንደ መለከቱን ነፋ፤ እስራኤላውያንም በእርሱ መሪነት ከኰረብታው ላይ አብረውት ወረዱ።


በተመሸጉ ከተሞችና በረጃጅም ግንቦች ላይ መለከትና ቀረርቶ የሚሰማበት ቀን ነው።


በጊብዓ ቀንደ መለከትን፥ በራማ እንቢልታን ንፉ፤ “ብንያም ሆይ! ከአንተ ጋር ነን እያላችሁ በቤትአዌን ላይ የማስጠንቀቂያውን ነጋሪት ድምፅ አሰሙ።”


መለከቱን ነፍተዋል ሁሉንም ነገር አዘጋጅተዋል፥ ነገር ግን ወደ ጦርነት የሚሄድ የለም፥ ቁጣዬ በብዙዎች ሁሉ ላይ ነውና።


እናንተ የብንያም ልጆች ሆይ! ክፉ ነገር ታላቅም ጥፋት ከሰሜን ይጐበኛልና ከኢየሩሳሌም ውስጥ ለደህንነታችሁ ሽሹ፥ በቴቁሔ መለከቱን ንፉ፥ በቤትሐካሪም ላይ ምልክት አንሡ።


“ለእስራኤል ልጆች እንዲህ ብለህ ተናገር፦ በሰባተኛው ወር፥ ወሩ በገባ በመጀመሪያው ቀን ፈጽሞ የምታርፉበት፥ በመለከት ድምፅ መታሰቢያ የምታውጁበት፥ የተቀደሰ ጉባኤ የምታደርጉበት ይሁንላችሁ።


እነሆም፥ ጌታ በእኛ ላይ አለቃ ነው፥ መለከቱንም የሚነፉ ካህናቱ ከእኛ ጋር ናቸው፥ በእናንተም ላይ የጦርነት ማስጠንቀቅያ ድምፅ ያሰማሉ። የእስራኤል ልጆች ሆይ! አይበጃችሁምና ከአባቶቻችሁ አምላክ ከጌታ ጋር አትዋጉ።”


ስለዚህ፥ እነሆ፥ በአሞን ልጆች ከተማ በረባት ላይ የጦርነት ውካታን የማሰማበት ቀኖች ይመጣሉ፥ ይላል ጌታ፤ የፍርስራሽ ክምርም ትሆናለች፥ ሴቶች ልጆችዋም በእሳት ይቃጠላሉ፥ እስራኤልም የወረሱትን ይወርሳል፥ ይላል ጌታ።


“ከግብጽ ያወጣህ አምላክህ ጌታ ከአንተ ጋር ነውና፥ ጠላቶችህን ለመውጋት ወደ ጦርነት ስትሄድ፥ ሠረገሎችንና ፈረሶችን ከአንተ የሚበልጥ ሠራዊትንም በምታይበት ጊዜ አትፍራቸው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios