ሦስተኛም ቀን በሆነ ጊዜ እጅግ ቆስለው ሳሉ የዲና ወንድሞች የያዕቆብ ልጆች ስምዖንና ሌዊ እየራሳቸው ሰይፋቸውን ይዘው ሳይፈሩ ወደ ከተማ ገቡ
ኢያሱ 5:8 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሕዝቡም ሁሉ ፈጽመው በተገረዙ ጊዜ እስኪድኑ ድረስ በሰፈር ውስጥ በየስፍራቸው ተቀመጡ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሕዝቡ ሁሉ ከተገረዙ በኋላ ቍስሉ እስኪሽር ድረስ እዚያው በሰፈሩበት ቦታ ቈዩ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሕዝቡም ሁሉ ፈጽመው በተገረዙ ጊዜ እስኪድኑ ድረስ በሰፈር ውስጥ በየስፍራቸው ተቀመጡ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሰዎች ሁሉ ከተገረዙ በኋላ ቊስላቸው እስኪድን ድረስ በሰፈር ቈዩ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በተገረዙም ጊዜ እስኪድኑ ድረስ በሰፈር ውስጥ ተቀመጡ። |
ሦስተኛም ቀን በሆነ ጊዜ እጅግ ቆስለው ሳሉ የዲና ወንድሞች የያዕቆብ ልጆች ስምዖንና ሌዊ እየራሳቸው ሰይፋቸውን ይዘው ሳይፈሩ ወደ ከተማ ገቡ
እግዚአብሔርም ኢያሱን፦ ዛሬ የግብፅን ነውር ከእናንተ ላይ አንከባልያለሁ አለው፥ ስለዚህ የዚያን ስፍራ ስም እስከ ዛሬ ድረስ ጌልገላ ተብሎ ተጠራ።