ኢያሱ 10:3 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለዚህም የኢየሩሳሌም ንጉሥ አዶኒጼዴቅ ወደ ኬብሮን ንጉሥ ወደ ሆሃም፥ ወደ የርሙት ንጉሥም ወደ ጲርአም፥ ወደ ለኪሶ ንጉሥም ወደ ያፊዓ፥ ወደ አዶላም ንጉሥም ወደ ዳቤር ልኮ፦ ወደ እኔ ውጡ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ የኢየሩሳሌም ንጉሥ አዶኒጼዴቅ፣ ሆሃም ወደተባለው የኬብሮን ንጉሥ ጲርአም ወደተባለው የያርሙት ንጉሥ፣ ያፊዓ ወደተባለው የለኪሶ ንጉሥና ዳቤር ወደተባለው የዔግሎን ንጉሥ በመላክ፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህም የኢየሩሳሌም ንጉሥ አዶኒጼዴቅ ወደ ኬብሮን ንጉሥ ወደ ሆሃም፥ ወደ የርሙት ንጉሥም ወደ ጲርአም፥ ወደ ለኪሶ ንጉሥም ወደ ያፊዓ፥ ወደ ዔግሎም ንጉሥም ወደ ዳቤር እንዲህ ብሎ ላከ፦ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ የኢየሩሳሌሙ ንጉሥ አዶኒጼዴቅ ሆሃም ተብሎ ለሚጠራው ለኬብሮን ንጉሥ፥ ፒራም ለተባለው ለያርሙት ንጉሥ፥ ያፊዓ ለተባለው ለላኪሽ ንጉሥና ደቢር ለተባለው ለዔግሎን ንጉሥ እንዲህ የሚል መልእክት ላከ፦ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስለዚህም የኢየሩሳሌም ንጉሥ አዶኒቤዜቅ ወደ ኬብሮን ንጉሥ ወደ ኤላም፥ ወደ የርሙት ንጉሥም ወደ ፊዶን፥ ወደ ለኪስ ንጉሥም ወደ ኤፍታ፥ ወደ አዶላም ንጉሥም ወደ ዳቤር ልኮ፥ |
የይሁዳም ንጉሥ ሕዝቅያስ “በድያለሁ፤ ከእኔ ተመለስ፤ የምትጭንብኝን ሁሉ እሸከማለሁ፤” ብሎ ወደ አሦር ንጉሥ ወደ ለኪሶ ላከ። የአሦርም ንጉሥ በይሁዳ ንጉሥ በሕዝቅያስ ላይ ሦስት መቶ መክሊት ብርና ሠላሳ መክሊት ወርቅ ጫነበት።
የአሦርም ንጉሥ ተርታንንና ራፌስን ራፋስቂስንም ከብዙ ሠራዊት ጋር ከለኪሶ ወደ ንጉሡ ወደ ሕዝቅያስ ወደ ኢየሩሳሌም ላከ። ወጥተውም ወደ ኢየሩሳሌም መጡ፤ በመጡም ጊዜ በአጣቢው እርሻ መንገድ ባለችው በላይኛይቱ ኩሬ መስኖ አጠገብ ቆሙ።
በለኪሶ የምትቀመጪ ሆይ፥ ሰረገላውን ለፈረስ እሰሪ፥ እርስዋ ለጽዮን ሴት ልጆች የኃጢአት መጀመሪያ ነበረች፥ የእስራኤል በደል በአንቺ ዘንድ ተገኝቶአልና።
በደቡብም በኩል ወጡ፥ ወደ ኬብሮንም ደረሱ፤ በዚያም የዔናቅ ልጆች አኪመን፥ ሴሲ፥ ተላሚ ነበሩ። ኬብሮንም በግብፅ ካለችው ከጣኔዎእ በፊት ሰባት ዓመት ተሠርታ ነበር።
እንዲህም ሆነ፥ የኢየሩሳሌም ንጉሥ አዶኒጼዴቅ ኢያሱ ጋይን እንደ ያዘ ፈጽሞም እንዳጠፋት፥ በኢያሪኮና በንጉሥዋም ያደረገውን እንዲሁ በጋይና በንጉሥዋ እንዳደረገ፥ የገባዖንም ሰዎች ከእስራኤል ጋር ሰላም እንዳደረጉ በመካከላቸውም እንደ ሆኑ በሰማ ጊዜ፥
እንዲህም አደረጉ፥ አምስቱንም ነገሥታት፥ የኢየሩሳሌምን ንጉሥ የኬብሮንንም ንጉሥ የየርሙትንም ንጉሥ የለኪሶንም ንጉሥ የአዶላምንም ንጉሥ፥ ከዋሻው ወደ እርሱ አወጡአቸው።
አምስቱም የአሞራውያን ነገሥታት፥ የኢየሩሳሌም ንጉሥ፥ የኬብሮን ንጉሥ፥ የየርሙት ንጉሥ፥ የለኪሶ ንጉሥ፥ የአዶላም ንጉሥ፥ ከሠራዊቶቻቸው ሁሉ ጋር ተሰብስበው ወጡ፥ ከገባዖንም ጋር ሊጋጠሙ ከበቡአት።
የኬብሮንም ስም አስቀድሞ ቂርያትአርባቅ ትባል ነበር፥ ይህም አርባቅ በዔናቅ ሰዎች መካከል ከሁሉ ከፍ ያለ ነበረ። ምድሪቱም ከውጊያ ዐረፈች።
በኢየሩሳሌም የተቀመጡትን ኢያቡሳውያንን ግን የይሁዳ ልጆች ሊያሳድዱአቸው አልተቻላቸውም፥ ኢያቡሳውያንም እስከ ዛሬ በይሁዳ ልጆች መካከል በኢየሩሳሌም ውስጥ ተቀምጠዋል።