መዝሙር 68:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ማቅ ለበስሁ መተረቻም ሆንሁላቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጌታ እንዲህ ሲል ቃሉን አስተላለፈ፤ ትእዛዙን የሚያውጁትም ብዙ ሰራዊት ናቸው፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንስሶችህ በውስጡ አደሩ፥ አቤቱ፥ በቸርነትህ ለድሆች አዘጋጀህ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ትእዛዝ ሰጠ፤ ብዙ ሴቶችም ዜናውን አሠራጩ፤ |
እርሱም ጸጋን ሰጠ፤ ከቤተ ሰቦቹም ሐዋርያትን፥ ከእነርሱም ነቢያትንና የወንጌል ሰባኪዎችን፥ ጠባቂዎችንና መምህራንን ሾመ።
ዲቦራም ልካ ከቃዴስ ንፍታሌም የአቢኒሔምን ልጅ ባርቅን ጠርታ እንዲህ አለችው፥ “የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ብሎ ያዘዘህ አይደለምን? ሄደህ ወደ ታቦር ተራራ ውጣ፤ ከአንተም ጋር ከንፍታሌምና ከዛብሎን ልጆች ዐሥር ሺህ ሰዎች ውሰድ፤
እንዲህም ሆነ፤ ዳዊት ፍልስጥኤማዊውን ገድሎ በተመለሰ ጊዜ፥ እየዘመሩና እየዘፈኑ፥ እልልም እያሉ ከበሮና አታሞ ይዘው ዳዊትን ሊቀበሉ ሴቶች ከእስራኤል ከተሞች ሁሉ ወጡ።