ቃሉን ልኮ ያቀልጠዋል፤ ነፋሱን ያነፍሳል፥ ውኆችንም ያፈስሳል።
ለእግዚአብሔር በምስጋና ዘምሩ፤ ለአምላካችንም በመሰንቆ ምስጋና አቅርቡ።
ለጌታ በምስጋና ዘምሩ፥ ለአምላካችንም በመሰንቆ ዘምሩ፥
ለእግዚአብሔር የምስጋና መዝሙር ዘምሩ፤ በገና እየደረደራችሁ ለአምላካችን ዘምሩ።
ድሆች ይዩ ደስም ይበላቸው፤ እግዚአብሔርን ፈልጉት፥ ነፍሳችሁም ትድናለች።
ፈጣሪያችን እግዚአብሔር ከፍ ከፍ አለ፥ ከእግሩ መረገጫ በታችም ይሰግዱለታል።