ከበደላቸው ጎዳና ተቀበላቸው፥ በኀጢአታቸው ተሠቃይተዋልና።
ምድር ተከፍታ ዳታንን ዋጠች፤ የአቤሮንን ወገን ሰለቀጠች።
ምድርም ተከፈተች ዳታንንም ዋጠችው፥ የአቤሮንንም ወገን ደፈነች፥
ምድርም ተከፍታ ዳታንን ዋጠች፤ አቤሮንንና ቤተሰቡንም ከደነቻቸው።
ማኅበሩም በሞቱ ጊዜ ምድሪቱ አፍዋን ከፍታ ከቆሬ ጋር ዋጠቻቸው፤ በዚያም ጊዜ እሳቲቱ ሁለት መቶ አምሳውን ሰዎች አቃጠለቻቸው፤ እነርሱም ለምልክት ሆኑ።
በእስራኤልም ሁሉ መካከል ምድር አፍዋን ከፍታ እነርሱንና ቤተ ሰቦቻቸውን፥ ድንኳኖቻቸውንም፥ ለእነርሱም የነበራቸውን ሁሉ በዋጠቻቸው በሮቤል ልጅ በኤልያብ ልጆች በዳታንና በአቤሮን ያደረገውን ሁሉ፤