የሠራውን ድንቅ ዐስቡ፥ ተአምራቱን፥ የአፉንም ፍርድ።
ለዘላለም እንዳትናወጥ፣ ምድርን በመሠረቷ ላይ አጸናት።
ለዘለዓለም እንዳትናወጥ ምድርን በመሠረትዋ ላይ መሠረታት።
ምድርን በመሠረትዋ ላይ አጽንተህ አቆምሃት፤ ከቶም አትናወጥም።
ሰማይን በባዶ ስፍራ ላይ ይዘረጋል፥ ምድሪቱንም አንዳች አልባ ያንጠለጥላል።
ባላስብሽ፥ ምላሴ በጕሮሮዬ ይጣበቅ፤ ከደስታዬ ሁሉ በላይ ኢየሩሳሌምን ባልወድድ።
አቤቱ፥ አንተን ታመንሁ፤ ለዘለዓለም አልፈር፤ ጠላቶቼ በእኔ አይሣቁብኝ።
ለሚፈሩት ችግር የለባቸውምና ቅዱሳን ሁሉ፥ እግዚአብሔርን ፍሩት።
ጌታ እግዚአብሔር ተበቃይ ነው፥ እግዚአብሔር በግልጥ ተበቃይ ነው።
እግዚአብሔርን የምትወድዱ፥ ክፋትን ጥሉ፤ እግዚአብሔር የጻድቃኑን ነፍሶች ይጠብቃል፥ ከኃጥኣንም እጅ ያድናቸዋል።
ለባሕርም ዳርቻን በወሰነ ጊዜ ውኃ ከትእዛዙ እንዳያልፍ፥ የምድርን መሠረት ባጸና ጊዜ፥
ትውልድ ያልፋል፥ ትውልድም ይመጣል፤ ምድር ግን ለዘለዓለም ጸንታ ትኖራለች።
የጌታው ቀን ግን እንደ ሌባ ሆኖ ይመጣል፤ በዚያም ቀን ሰማያት በታላቅ ድምፅ ያልፋሉ፤ የሰማይም ፍጥረት በትልቅ ትኵሳት ይቀልጣል፤ ምድርም በእርስዋም ላይ የተደረገው ሁሉ ይቃጠላል።
ታላቅና ነጭ ዙፋንን በእርሱም ላይ የተቀመጠውን አየሁ፤ ምድርና ሰማይም ከፊቱ ሸሹ፤ ስፍራም አልተገኘላቸውም።
ሰማይም እንደ መጽሐፍ ተጠቅልሎ አለፈ፤ ተራራዎችና ደሴቶችም ሁሉ ከስፍራቸው ተወሰዱ።
ችግረኛውን ከመሬት ያነሣዋል፤ ምስኪኑንም ከጕድፍ ያነሣዋል፤ ከሕዝቡ መኳንንት ጋር ያስቀምጠው ዘንድ፥ የክብርንም ዙፋን ያወርሰው ዘንድ።