የሜዳ ቍጥቋጦ ሁሉ በምድር ላይ ከመኖሩ በፊት፥ የሜዳውም ቡቃያ ሁሉ ከመብቀሉ በፊት፥ አዳምም ከመፈጠሩ በፊት፥ እግዚአብሔር አምላክ በምድር ላይ አላዘነበም ነበር፤ ምድርንም የሚሠራባት ሰው አልነበረም።
መዝሙር 104:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሰው ግፍ ያደርግባቸው ዘንድ አልተወም፥ ስለ እነርሱም ነገሥታቱን ገሠጸ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከምድር ምግብን ታወጣ ዘንድ፣ ለእንስሳት ሣርን፣ ለሰው ልጆች ሥራ ዕፀዋትን ታበቅላለህ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንጀራን ከምድር ያወጣ ዘንድ ሣርን ለእንስሳ፥ ለምለሙንም ለሰው ልጆች ጥቅም ያበቅላል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሣርን ለእንስሶች ታበቅላለህ፤ አትክልትንም ለሰው ልጆች ጥቅም እንዲውል ታደርጋለህ፤ በዚህ ዐይነት ሰው ምግብ የሚሆነውን ዘርቶ ይሰበስባል። |
የሜዳ ቍጥቋጦ ሁሉ በምድር ላይ ከመኖሩ በፊት፥ የሜዳውም ቡቃያ ሁሉ ከመብቀሉ በፊት፥ አዳምም ከመፈጠሩ በፊት፥ እግዚአብሔር አምላክ በምድር ላይ አላዘነበም ነበር፤ ምድርንም የሚሠራባት ሰው አልነበረም።
እግዚአብሔር አምላክም ለማየት ደስ የሚያሰኘውን፥ ለመብላትም መልካም የሆነውን ዛፍ ሁሉ ደግሞ ከምድር አበቀለ፤ በገነትም መካከል የሕይወትን ዛፍ፥ መልካምንና ክፉን የሚያሳየውንና የሚያስታውቀውንም ዛፍ አበቀለ።
አክዓብም አብድዩን፥ “በሀገሩ መካከል ወደ ውኃ ምንጭ ሁሉና ወደ ፈፋ ሁሉ ና እንሂድ፤ እንስሶችም ሁሉ እንዳይጠፉ ፈረሶችንና በቅሎችን የምናድንበት ሣር ምናልባት እናገኝ እንደ ሆነ” አለው።
እናንተ የምድር እንስሶች ሆይ! የምድረ በዳው ማሰማርያ ለምልሞአልና፥ ዛፉም ፍሬውን አፍርቶአልና፥ በለሱና ወይኑም ኀይላቸውን ሰጥተዋልና አትፍሩ።