ሴቲቱም ዛፉ ለመብላት ያማረ እንደሆነ፥ ለዐይንም ለማየት እንደሚያስጐመጅ፥ መልካምንም እንደሚያሳውቅ ባየች ጊዜ፥ ከፍሬው ወሰደችና በላች፤ ለባልዋም ደግሞ ሰጠችው፤ እርሱም ከእርስዋ ጋር በላ።
ምሳሌ 9:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “የተሸሸገ እንጀራን አሰማምረህ ዳስስ። ጣፋጭ የስርቆት ውኃንም ጠጣ፥” አዲሱ መደበኛ ትርጒም “የስርቆት ውሃ ይጣፍጣል፤ ተሸሽገው የበሉት ምግብ ይጥማል።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “የስርቆት ውኃ ይጣፍጣል፥ የተሸሸገም እንጀራ ደስ ያሰኛል።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ሰርቀው የሚጠጡት ውሃ ይጣፍጣል፤ ተሸሽገው የሚበሉትም እንጀራ ያስደስታል።” |
ሴቲቱም ዛፉ ለመብላት ያማረ እንደሆነ፥ ለዐይንም ለማየት እንደሚያስጐመጅ፥ መልካምንም እንደሚያሳውቅ ባየች ጊዜ፥ ከፍሬው ወሰደችና በላች፤ ለባልዋም ደግሞ ሰጠችው፤ እርሱም ከእርስዋ ጋር በላ።
ያችም ትእዛዝ ለኀጢአት ምክንያት ሆነቻት፤ ምኞትንም ሁሉ አመጣችብኝ፤ ቀድሞ ግን ኦሪት ሳትሠራ ኀጢአት ሙት ነበረች።