ለተስፋ ይሆንህ ዘንድ ልጅህን ግረፍ፥ ለመሳደብ ግን እጅህን አታንሣ፥
ገና ተስፋ ሳለ፣ ልጅህን ሥርዐት አስይዘው፤ ሲሞት ዝም ብለህ አትየው።
ተስፋ ገና ሳለች ልጅህን ገሥጽ፥ መሞቱንም አትሻ።
የመመለስ ተስፋ ሳላቸው ልጆችህን በልጅነታቸው ቅጣቸው፤ ባትቀጣቸው ግን ለጥፋት አሳልፈህ እንደ ሰጠሃቸው ይቈጠራል።
በበትር ከመምታት የሚራራ ሰው ልጁን ይጠላል፤ ልጁን የሚወድድ ግን በጥንቃቄ ይቀጣዋል።
ዐሳበ ክፉ ሰው ብዙ ያጠፋል፤ ጽኑ ደፋር ቢሆን ግን ነፍሱን ይጨምራል።
አለማወቅ የጐልማሳን ልብ ከፍ ከፍ አደረገች፤ በትርና ተግሣጽ ከእርሱ ርቀዋልና።
“ማንም ሰው ለአባቱ ቃልና ለእናቱ ቃል የማይታዘዝ፥ ቢገሥጹትም የማይሰማቸው ትዕቢተኛና ዐመፀኛ ልጅ ቢኖረው፥