ምሳሌ 16:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በልቡ የታበየ ሁሉ በእግዚአብሔር ዘንድ ርኩስ ነው። በዐመፃ እጅን በእጅ የሚመታ አይነጻም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ሁሉንም ነገር ለራሱ ዐላማ ሠርቷል፤ ክፉዎችንም እንኳ ለጥፋት ቀን አዘጋጅቷል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታ ሁሉን ለእርሱ ለራሱ ፈጠረ፥ ኀጥእን ደግሞ ለክፉ ቀን። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር የፈጠረው ነገር ሁሉ ምክንያት አለው፤ የክፉዎችም መጨረሻ ጥፋት ነው። |
ለአሞራዎችም ምግብ ሆኖ ተሰጥቶአል በድን ሆኖ እንደሚቈይም እርሱ ራሱ ያውቃል። የጨለማ ቀንም እንደ አውሎ ነፋስ ትወስደዋለች።
የሠራው ሥራ ሁሉ በጊዜው መልካም ነው፤ እግዚአብሔርም ከጥንት ጀምሮ እስከ ፍጻሜ ድረስ የሠራውን ሥራ ሰው መርምሮ እንዳያገኝ ዘለዓለምነትን በልቡ ሰጠው።
እግዚአብሔርም ኀይሉን የሚገልጽበትን ቅጣቱን ሊያሳይ ቢወድ፥ ትዕግሥቱን ካሳየ በኋላ ለማጥፋት የተዘጋጁትን ቍጣውን የሚገልጽባቸውን መላእክት ያመጣል።
ጌታ እግዚአብሔርን የሚያመልኩትን ከፈተና እንዴት እንዲያድን በደለኞችንም ይልቁንም በርኵስ ምኞት የሥጋን ፍትወት እየተከተሉ የሚመላለሱትን ጌትነትንም የሚንቁትን እየቀጣቸው ለፍርድ ቀን እንዴት እንዲጠብቅ ያውቃል። ደፋሮችና ኵሩዎች ሆነው ሥልጣን ያላቸውን ሲሳደቡ አይንቀጠቀጡም፤