ምሳሌ 16:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእግዚአብሔር ፍርድ እንደ ሚዛን ውልብልቢት ነው፤ ሥራውም የከረጢት ደንጊያ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሐቀኛ መስፈሪያና ሚዛን ከእግዚአብሔር ናቸው፤ በከረጢት ውስጥ ያሉት መመዘኛዎችም ሁሉ ሥራዎቹ ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እውነተኛ ሚዛንና መመዘኛ የጌታ ናቸው፥ የከረጢት መመዘኛዎች ሁሉ የእርሱ ሥራ ናቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሚዛንና መስፈሪያ ትክክል እንዲሆኑ፥ ለሽያጭ የሚቀርቡት ዕቃዎች ሁሉ ሚዛናቸው የተስተካከለ እንዲሆን የእግዚአብሔር ትእዛዝ ነው። |
“እህልን እንሸጥ ዘንድ መባቻው መቼ ያልፋል? የኢፍ መስፈሪያውንም እያሳነስን፥ ሰቅሉንም እያበዛን፥ በሐሰተኛም ሚዛን እያታለልን፥