La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ምሳሌ 14:27 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

የእግዚአብሔር ትእዛዝ የሕይወት ምንጭ ነው። ሰዎችንም ከሞት ወጥመድ እንዲያመልጡ ያደርጋል።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እግዚአብሔርን መፍራት የሕይወት ምንጭ ነው፤ ሰውን ከሞት ወጥመድ ያድነዋል።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ሰው ከሞት ወጥመድ ያመልጥ ዘንድ ጌታን መፍራት የሕይወት ምንጭ ነው።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እግዚአብሔርን መፍራት የሕይወት ምንጭ ነው፤ ስለዚህ ከሞት ወጥመድ ለማምለጥ ከፈለግህ እግዚአብሔርን ፍራ።

Ver Capítulo



ምሳሌ 14:27
11 Referencias Cruzadas  

በፀ​ሐይ ውስጥ ድን​ኳ​ኑን አደ​ረገ፥ እር​ሱም እንደ ሙሽራ ከእ​ል​ፍኙ ይወ​ጣል፤ በመ​ን​ገዱ እን​ደ​ሚ​ራ​መድ አር​በኛ ደስ ይለ​ዋል።


እግዚአብሔርን መፍራት ዘመንን ያረዝማል፤ የኃጥኣን ዕድሜ ግን ያጥራል።


የብልህ ሰው ሕግ የሕይወት ምንጭ ነው። ማስተዋል የሌለው ግን በኀጢአት ይሞታል።


እግዚአብሔርን ለሚፈራ ጽኑዕ ተስፋ አለው፥ ለልጆቹም መጠጊያን ይተዋል።


የንጉሥ ክብር በሕዝብ ብዛት ነው፤ የገዥ ውድቀት ግን በሕዝብ ማነስ ነው።


እግዚአብሔርን መፍራት የሰው ሕይወት ነው፤ የማይፈራው ግን ዕውቀት በሌለበት ቦታ ውስጥ ይኖራል።


እሾህና ወጥመድ በጠማማ ሰው መንገድ ናቸው፤ ነፍሱን የሚጠብቅ ግን ከእነርሱ ያመልጣል።


እኔም ከሞት ይልቅ የመ​ረ​ረች ነገ​ርን አገ​ኘሁ፤ እር​ስ​ዋም ልብዋ ወጥ​መ​ድና መረብ የሆነ፥ በእ​ጆ​ች​ዋም ማሰ​ሪያ ያላት ሴት ናት፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት ደግ የሆነ ከእ​ርሷ ያመ​ል​ጣል። ኀጢ​አ​ተኛ ግን ይጠ​መ​ድ​ባ​ታል።


በድ​ኅ​ነ​ታ​ችን መዝ​ገብ በሕግ ይሰ​በ​ስ​ቡ​አ​ቸ​ዋል፤ ጥበ​ብና ምክር፥ ጽድ​ቅም ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ናቸው፤ እነ​ዚ​ህም የጽ​ድቅ መዝ​ገ​ቦች ናቸው።


አለኝም “ተፈጽሞአል፤ አልፋና ዖሜጋ፥ መጀመሪያውና መጨረሻው እኔ ነኝ። ለተጠማ ከሕይወት ውሃ ምንጭ እንዲያው እኔ እሰጣለሁ።