ምሳሌ 11:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ቸር ሰው ለነፍሱ መልካም ያደርጋል፤ ጨካኝ ግን ሥጋውን ይጐዳል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ደግ ሰው ራሱን ይጠቅማል፤ ጨካኝ ግን በራሱ ላይ መከራ ያመጣል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ቸር ሰው ለራሱ መልካም ያደርጋል፥ ጨካኝ ግን ራሱን ይጐዳል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ርኅሩኅ ብትሆን ራስህን ትጠቅማለህ፤ ጨካኝ ብትሆን ግን ራስህን ትጐዳለህ። |
መማለጃን የሚቀበል ራሱን ያጠፋል፤ መማለጃ መቀበልን የሚጠላ ግን ይድናል። በምጽዋትና በእምነት ኀጢአት ይሰረያል። እግዚአብሔርንም በመፍራት ክፉ ሁሉ ይወገዳል።
ለድሃ የሚራራ እርሱ ይበላል እንጀራውን ለድሃ ሰጥቶአልና። ለሰጠው ሀብታምም የሚከፍል አይደለምና። መማለጃን የሰጠ ሰው ድል መንሣትንና ሞገስን ያገኛል፥ ነገር ግን የተቀበለውን ነፍስ ያጠፋል።
አንድ ሰው ብቻውን አለ፥ ሁለተኛም የለውም፥ ልጅም ሆነ ወንድም የለውም፤ ለድካሙ ግን መጨረሻ የለውም፥ ዐይኖቹም ከባለጠግነት አይጠግቡም። ለማን እደክማለሁ? ሰውነቴንስ ከደስታ ለምን እነፍጋታለሁ? ይላል። ይህም ደግሞ ከንቱ ነገር፥ ክፉም ጥረት ነው።
ጻድቅ ሰው እንደጠፋ አያችሁ፤ ይህንም በልባችሁ አላሰባችሁም፤ ጻድቃን ሰዎች ይወገዳሉ፤ ጻድቅም ከክፋት ፊት እንደ ተወገደ ማንም አያስተውልም።
ስጡ፥ ይሰጣችኋልም፤ የሞላና የበዛ፥ የተትረፈረፈም መልካም መስፈሪያ በዕቅፋችሁ ይሰጡአችኋል፤ በሰፈራችሁበትም መስፈሪያ ይሰፍሩላችኋል።”