ምሳሌ 10:27 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርን መፍራት ዘመንን ያረዝማል፤ የኃጥኣን ዕድሜ ግን ያጥራል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔርን መፍራት ዕድሜን ያረዝማል፤ የክፉዎች ዕድሜ ግን በዐጭር ይቀጫል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታን መፍራት ዘመንን ታረዝማለች፥ የከፉዎች ዕድሜ ግን ታጥራለች። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔርን መፍራት ዕድሜን ያረዝማል፤ ክፉዎች ግን ያለ ዕድሜያቸው በሞት ይቀጫሉ። |
ረጅም ዕድሜና የሕይወት ዘመን በቀኝዋ ነው። ባለጠግነትና ክብርም በግራዋ፥ ከአፏ ጽድቅ ይወጣል። ሕግንና ምጽዋትንም በአንደበትWa ትለብሳለች።
ቆቅ ጮኸች፤ ያልወለደችውንም ዐቀፈች፤ በዐመፅ ባለጠግነትን የሚሰበስብ ሰውም እንደዚሁ ነው፤ በእኩሌታ ዘመኑ ይተወዋል፤ በፍጻሜውም ሰነፍ ይሆናል።
እግዚአብሔርም፦ አንተ ሰነፍ! በዚች ሌሊት ነፍስህን ከሥጋህ ለይተው ይወስዷታል፤ እንግዲህ ያጠራቀምኸው ለማን ይሆናል? አለው።
እግዚአብሔር ለእነርሱና ከእነርሱም በኋላ ለዘራቸው ወተትና ማር የምታፈስሰውን ምድር ይሰጣቸው ዘንድ ለአባቶቻችሁ በማለላቸው ምድር ላይ ዕድሜያችሁ እንዲረዝም።