ለአሮንም ልጆች የመማፀኛውን ከተሞች፥ ኬብሮንን፥ ልብናንና መሰማርያዋን፥ ሴልናንና መሰማሪያዋን፤ ኤስትሞዓንና መሰማሪያዋን ሰጡ።
ዘኍል 35:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የምትሰጡአቸውም ስድስቱ ከተሞች የመማፀኛ ከተሞች ይሁኑላችሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነዚህ ለሌዋውያኑ የምትሰጧቸው ስድስት ከተሞች መማፀኛ ከተሞቻችሁ ይሆናሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የምትሰጡአቸውም ስድስቱ ከተሞች የመማፀኛ ከተሞች ይሁኑላችሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስድስት ከተሞችን ምረጡ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የምትሰጡአቸውም ስድስቱ ከተሞች የመማፀኛ ከተሞች ይሁኑላችሁ። |
ለአሮንም ልጆች የመማፀኛውን ከተሞች፥ ኬብሮንን፥ ልብናንና መሰማርያዋን፥ ሴልናንና መሰማሪያዋን፤ ኤስትሞዓንና መሰማሪያዋን ሰጡ።
ነፍሰ ገዳዩ በማኅበሩ ፊት ለፍርድ እስከሚቆም ድረስ እንዳይሞት፥ ከተሞቹ ከደም ተበቃይ የመማፀኛ ከተሞች ይሁኑላችሁ።
በዮርዳኖስ ማዶ ሦስት ከተሞችን ትለያላችሁ፤ በከነዓንም ምድር ሦስት ከተሞችን ትለያላችሁ፤ የመማፀኛ ከተሞችም ይሆናሉ።
ለሌዋውያንም ከተሞችን ትሰጣላችሁ፤ ከምትሰጡአቸውም ከተሞች ስድስቱ ነፍሰ ገዳይ የሚሸሽባቸው የመማፀኛ ከተሞች ናቸው፤ ከእነዚህ ሌላ አርባ ሁለት ከተሞችን ትሰጣላችሁ።
በማኅበሩ ፊት እስኪቆምና እስኪመረመር ድረስ ባለደሙ እንዳይገድለው ሳያውቅ ሰውን የገደለ ወደዚያ እንዲማፀን፥ ለእስራኤል ልጆች ሁሉ፥ በመካካላቸውም ለሚቀመጥ መጻተኛ የተመረጡ ከተሞች እነዚህ ናቸው።