ዘኍል 10:35 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ባረፈም ጊዜ፥ “አቤቱ፥ ወደ እስራኤል እልፍ አእላፋት ተመለስ” ይል ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ታቦቱ ለጕዞ በተነሣ ጊዜ ሁሉ ሙሴ፣ “እግዚአብሔር ሆይ፤ ተነሥ! ጠላቶችህ ይበተኑ፤ የሚጠሉህም ከፊትህ ይሽሹ” ይል ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሙሴም ታቦቱ በተጓዘ ጊዜ ሁሉ እንዲህ ይል ነበር፦ “አቤቱ፥ ተነሣ፥ ጠላቶችህም ይበተኑ፥ የሚጠሉህም ከፊትህ ይሽሹ።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የቃል ኪዳኑ ታቦት በተንቀሳቀሰ ጊዜ ሁሉ ሙሴ “እግዚአብሔር ሆይ! ተነሥ፤ ጠላቶችህ ይበተኑ፤ የሚጠሉህም ሁሉ ከፊትህ ይባረሩ!” ይል ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሙሴም ታቦቱ በተጓዘ ጊዜ፦ አቤቱ፥ ተነሣ፥ ጠላቶችህም ይበተኑ፥ የሚጠሉህም ከፊትህ ይሽሹ ይል ነበር። |
ሰይፌን እንደ መብረቅ እስላታለሁ፤ እጄም ፍርድን ትይዛለች፤ ለሚጠሉኝም ፍዳቸውን እከፍላለሁ፤ ጠላቶችንም እበቀላለሁ።
የሚጠሉትን ለማጥፋት በፊታቸው ብድራት ይመልስባቸዋል፤ ለሚጠላው አይዘገይም፤ ነገር ግን በፊቱ ብድራትን ይመልስበታል።
ሕዝቡም ወደ ሰፈር በተመለሱ ጊዜ የእስራኤል ሽማግሌዎች፥ “ዛሬ እግዚአብሔር በፍልስጥኤማውያን ፊት ስለምን ጣለን? በፊታችን እንድትሄድ፥ ከጠላቶቻችንም እጅ እንድታድነን፥ የእግዚአብሔርን የቃል ኪዳኑን ታቦት ከሴሎ እናምጣ” አሉ።