በዘጠኝ ሰዓትም ኢየሱስ “ኤሎሄ! ኤሎሄ! ላማ ሰበቅታኒ?” ብሎ በታላቅ ድምፅ ጮኸ፤ ትርጓሜውም “አምላኬ! አምላኬ! ለምን ተውኸኝ?” ማለት ነው።
ማርቆስ 15:35 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዚያም ከቆሙት ሰዎች ሰምተው “እነሆ፥ ኤልያስን ይጠራል፤” አሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚያ ቆመው ከነበሩት አንዳንዶቹ ይህን ሲሰሙ፣ “ኤልያስን ይጣራል” አሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚያ ቆመው ከነበሩት አንዳንዶቹ ይህን ሲሰሙ፥ “ኤልያስን ይጣራል” አሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚያም ቆመው ከነበሩት ሰዎች አንዳንዶቹ የእርሱን ጩኸት ሰምተው “እነሆ! ኤልያስን ይጠራል፤” አሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዚያም ከቆሙት ሰዎች ሰምተው፦ እነሆ፥ ኤልያስን ይጠራል አሉ። |
በዘጠኝ ሰዓትም ኢየሱስ “ኤሎሄ! ኤሎሄ! ላማ ሰበቅታኒ?” ብሎ በታላቅ ድምፅ ጮኸ፤ ትርጓሜውም “አምላኬ! አምላኬ! ለምን ተውኸኝ?” ማለት ነው።