ቀርቦም እጅዋን ይዞ አስነሣት፤ ንዳዱም ወዲያው ለቀቃትና አገለገለቻቸው።
ስለዚህም እርሱ ወደ ተኛችበት በመሄድ እጇን ይዞ አስነሣት፤ ትኵሳቱም ተዋት፤ ተነሥታም ታገለግላቸው ጀመር።
ስለዚህም እርሱ ወደ ተኛችበት በመሄድ እጇን ይዞ አስነሣት፤ ትኩሳቱም ተዋት፤ ተነሥታም ታገለግላቸው ጀመር።
ኢየሱስም ወደ እርስዋ ቀረበና እጅዋን ይዞ አስነሣት፤ ትኲሳቱም ወዲያው ለቀቃት፤ ተነሥታም አስተናገደቻቸው።
ቀርቦም እጅዋን ይዞ አስነሣት ንዳዱም ወዲያው ለቀቃትና አገለገለቻቸው።
ኢየሱስን እያገለገሉ ከገሊላ የተከተሉት ብዙ ሴቶች በሩቅ ሆነው ሲመለከቱ በዚያ ነበሩ፤
የስምዖንም አማት በንዳድ ታማ ተኝታ ነበር፤ ስለ እርስዋም ወዲያው ነገሩት።
ፀሐይም ገብቶ በመሸ ጊዜ፥ የታመሙትንና አጋንንት ያደረባቸውን ሁሉ ወደ እርሱ አመጡ፤
ከእርሱም ጋር ወደ ኢየሩሳሌም የወጡ ሌሎች ብዙዎች ሴቶች ነበሩ።
የብላቴናይቱንም እጅ ይዞ “ጣሊታ ቁሚ!” አላት፤ ፍችውም “አንቺ ብላቴና ተነሽ እልሻለሁ!” ነው።
እጁንም ለእርስዋ ሰጥቶ አስነሣት፤ ቅዱሳንንና ባልቴቶችንም ጠርቶ እርስዋን አድኖ ሰጣቸው።