እንዲህም አላቸው፥ “በስሜ እንደዚህ ያለውን ሕፃን የሚቀበል እኔን ይቀበላል፥ እኔንም የሚቀበል የላከኝን ይቀበላል፤ ራሱን ከሁሉ ዝቅ የሚያደርግ እርሱ ታላቅ ይሆናል።”
ሉቃስ 9:53 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነገር ግን አልተቀበሉትም፤ ፊቱን ወደ ኢየሩሳሌም አቅንቶ ነበርና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሕዝቡ ግን ወደ ኢየሩሳሌም እያመራ መሆኑን ስላወቁ አልተቀበሉትም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ነገር ግን ወደ ኢየሩሳሌም ሊሄድ ፊቱን አቅንቶ ስለ ነበረ የመንደሩ ሰዎች አልተቀበሉትም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነገር ግን እርሱ በዚያ አልፎ ወደ ኢየሩሳሌም የሚሄድ መሆኑን ዐውቀው ስለ ነበር የዚያች መንደር ሰዎች ሊቀበሉት አልፈለጉም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ፊቱም ወደ ኢየሩሳሌም እንደሚሄድ ስለ ነበረ አልተቀበሉትም። |
እንዲህም አላቸው፥ “በስሜ እንደዚህ ያለውን ሕፃን የሚቀበል እኔን ይቀበላል፥ እኔንም የሚቀበል የላከኝን ይቀበላል፤ ራሱን ከሁሉ ዝቅ የሚያደርግ እርሱ ታላቅ ይሆናል።”
ያቺ የሰማርያ ሴትም፥ “አንተ አይሁዳዊ ስትሆን፥ እኔም ሳምራዊት ስሆን እንዴት ከእኔ ዘንድ ውኃ ልትጠጣ ትለምናለህ?” አለችው፤ አይሁድ ከሳምራውያን ጋር በሥርዐት አይተባበሩም ነበርና።