ሉቃስ 7:36 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከፈሪሳውያንም አንዱ በእርሱ ዘንድ ምሳ እንዲበላ ለመነው፤ ወደ ፈሪሳዊውም ቤት ገብቶ በማዕድ ተቀመጠ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚህ በኋላ ከፈሪሳውያን አንዱ ምግብ ዐብሮት እንዲበላ ኢየሱስን ጋበዘው፤ እርሱም ወደ ፈሪሳዊው ቤት ሄዶ በማእድ ተቀመጠ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከፈሪሳውያንም አንዱ ኢየሱስን ከእርሱ ጋር እንዲበላ ለመነው፤ በፈሪሳዊው ቤትም ገብቶ በማዕድ ተቀመጠ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከፈሪሳውያን አንዱ ኢየሱስን ምሳ ጋበዘው፤ ኢየሱስም ወደ ፈሪሳዊው ቤት ገብቶ ምሳ ለመብላት ወደ ማእድ ቀረበ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከፈሪሳውያንም አንድ ከእርሱ ጋር ይበላ ዘንድ ለመነው፤ በፈሪሳዊው ቤትም ገብቶ በማዕድ ተቀመጠ። |
ከዚህም በኋላ ሄዶ ከፈሪሳውያን አለቆች ወደ አንዱ ቤት በሰንበት ቀን እህል ሊበላ ገባ፤ እነርሱ ግን ይጠባበቁት ነበር።
የሰው ልጅም እየበላና እየጠጣ መጣ፤ እናንተ ግን እነሆ፥ በላተኛና ወይን ጠጪ ሰው፥ የኃጥኣንና የቀራጮች ወዳጅ አላችሁት።
እነሆ፥ ከዚያች ከተማ ሰዎችም አንዲት ኀጢአተኛ ሴት በፈሪሳዊው ቤት በማዕድ እንደተቀመጠ ዐውቃ ሽቱ የሞላበት የአልባስጥሮስ ቢልቃጥ ገዝታ መጣች።