ሉቃስ 18:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዚያችም ከተማ አንዲት መበለት ነበረች፤ ዕለት ዕለትም ወደ እርሱ እየመጣች ከባለጋራዬ ፍረድልኝ ትለው ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚያችው ከተማ የምትኖር አንዲት መበለት ነበረች፤ እርሷም፣ ‘ከባላጋራዬ ጋራ ስላለብኝ ጕዳይ ፍረድልኝ’ እያለች ወደ እርሱ ትመላለስ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚያችም ከተማ አንዲት መበለት ነበረች፤ ወደ እርሱም እየመጣች ‘በባላጋራዬ ፊት ፍረድን ስጠኝ፤’ ትለው ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አንዲት መበለትም በዚያች ከተማ ትኖር ነበር፤ እርስዋ ወደ ዳኛው እየመጣች ‘ከባላጋራዬ ጋር ስላለኝ ክርክር ፍርድ ስጠኝ!’ ትለው ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዚያችም ከተማ አንዲት መበለት ነበረች፥ ወደ እርሱም እየመጣች፦ ከባላጋራዬ ፍረድልኝ ትለው ነበር። |