ሉቃስ 12:38 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከሌሊቱ በሁለተኛው ወይም በሦስተኛው ክፍል ቢመጣና እንዲሁ ቢያገኛቸው እነዚያ አገልጋዮች ብፁዓን ናቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከሌሊቱ በሁለተኛውም ሆነ በሦስተኛው ክፍል መጥቶ እንደዚያው ነቅተው ቢያገኛቸው፣ እነዚያ ባሮች ብፁዓን ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከሌሊቱም በሁለተኛው ወይም በሦስተኛው ክፍል መጥቶ እንዲሁ ቢያገኛቸው፥ እነዚያ ባርያዎች ብፁዓን ናቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጌታቸው በእኩለ ሌሊት ወይም ከእኩለሌሊት በኋላ በመጣ ጊዜ ነቅተውና ተግተው ሲጠብቁት የሚያገኛቸው አገልጋዮች የተባረኩ ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከሌሊቱም በሁለተኛው ወይም በሦስተኛው ክፍል መጥቶ እንዲሁ ቢያገኛቸው፥ እነዚያ ባሪያዎች ብፁዓን ናቸው። |
ነገር ግን ይህን ዕወቁ፤ ባለቤት ሌባ የሚመጣበትን ጊዜ ቢያውቅ ተግቶ በጠበቀ፥ ቤቱንም እንዲቈፍሩት ባልፈቀደም ነበር።