ሕዝቅኤልም ምልክት ይሆናችኋል፤ እርሱ እንደ አደረገ ሁሉ እናንተ ታደርጋላችሁ፤ ይህም በመጣ ጊዜ እኔ ጌታ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ።
ሉቃስ 11:30 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዮናስ ለነነዌ ሰዎች ምልክት እንደ ሆናቸው የሰው ልጅም ለዚች ትውልድ እንዲሁ ምልክት ይሆናታል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዮናስ ለነነዌ ሰዎች ምልክት እንደ ሆናቸው የሰው ልጅም ለዚህ ትውልድ ምልክት ይሆናል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዮናስ ለነነዌ ሰዎች ምልክት እንደ ሆናቸው፥ እንዲሁ ደግሞ የሰው ልጅ ለዚህ ትውልድ ምልክት ይሆናል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነቢዩ ዮናስ ለነነዌ ከተማ ሰዎች ምልክት እንደ ነበረ እንዲሁም የሰው ልጅ ለዚህ ትውልድ ምልክት ይሆናል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዮናስ ለነነዌ ሰዎች ምልክት እንደ ሆናቸው፥ እንዲሁ ደግሞ የሰው ልጅ ለዚህ ትውልድ ምልክት ይሆናል። |
ሕዝቅኤልም ምልክት ይሆናችኋል፤ እርሱ እንደ አደረገ ሁሉ እናንተ ታደርጋላችሁ፤ ይህም በመጣ ጊዜ እኔ ጌታ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ።
እኔ ግን ከምስጋናና ከኑዛዜ ቃል ጋር እሠዋልሃለሁ፤ የድኅነቴ አምላክ ሆይ! የተሳልሁትን ለአንተ እከፍላለሁ።”