La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




መሳፍንት 4:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ሲሣ​ራም ሰረ​ገ​ሎ​ቹን ሁሉ፥ ዘጠኝ መቶ የብ​ረት ሰረ​ገ​ሎች፥ ከእ​ር​ሱም ጋር የነ​በ​ሩ​ትን ሕዝ​ቡን ሁሉ ከአ​ሕ​ዛብ አሪ​ሶት ወደ ቂሶን ወንዝ ሰበ​ሰ​ባ​ቸው።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ዘጠኝ መቶ የብረት ሠረገሎችንና ከአሪሶት ሐጎይም እስከ ቂሶን ወንዝ ያለውን ሰራዊቱን በሙሉ አሰባሰበ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ዘጠኝ መቶ የብረት ሠረገሎችንና ከሐሮሼት ሐጎይም እስከ ቂሶን ወንዝ ያለውን ሠራዊቱን በሙሉ አሰባሰበ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ሲሣራም ዘጠኝ መቶ የብረት ሠረገሎችንና ከእርሱ ጋር የነበረውን ሠራዊት ሁሉ የአሕዛብ ይዞታ ከነበረችው ከሐሮሼት ወደ ቂሶን ወንዝ ሰበሰበ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ሲሣራም ሰረገሎቹን ሁሉ፥ ዘጠኝ መቶ የብረት ሰረገሎች፥ ከእርሱም ጋር የነበሩትን ሕዝቡን ሁሉ ከአሪሶት ወደ ቂሶን ወንዝ ሰበሰባቸው።

Ver Capítulo



መሳፍንት 4:13
7 Referencias Cruzadas  

ኤል​ያ​ስም ሕዝ​ቡን፥ “የበ​ዓ​ልን ነቢ​ያት ያዙ፤ ከእ​ነ​ርሱ አንድ ሰው እን​ኳን የሚ​ያ​መ​ልጥ አይ​ኑር፤” አላ​ቸው። ያዙ​አ​ቸ​ውም፤ ኤል​ያ​ስም ወደ ቂሶን ወንዝ ወስዶ፥ በዚያ እየ​ወጋ ጣላ​ቸው።


እነ​ር​ሱም፥ “ተራ​ራ​ማው የኤ​ፍ​ሬም ሀገር አይ​በ​ቃ​ንም፤ በሸ​ለ​ቆው ውስጥ ለሚ​ኖ​ሩት፥ በቤ​ት​ሳ​ንና በመ​ን​ደ​ሮ​ችዋ፥ በኢ​ይ​ዝ​ራ​ኤ​ልም ሸለቆ ለሚ​ኖ​ሩት ከነ​ዓ​ና​ው​ያን የተ​መ​ረጡ ፈረ​ሶ​ችና ሰይፍ አሏ​ቸው” አሉት።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከይ​ሁዳ ጋር ነበረ፤ ይሁ​ዳም ተራ​ራ​ማ​ውን ሀገር ወረሰ፤ በሸ​ለ​ቆው የሚ​ኖ​ሩ​ትን ግን የብ​ረት ሰረ​ገ​ሎች ነበ​ሩ​አ​ቸ​ውና ሊወ​ር​ሳ​ቸው አል​ቻ​ለም።


የአ​ቢ​ኒ​ሔ​ምም ልጅ ባርቅ ወደ ታቦር ተራራ እንደ ወጣ ለሲ​ሣራ ነገ​ሩት።


እኔም የኢ​ያ​ቢ​ንን ሠራ​ዊት አለቃ ሲሣ​ራን፥ ሰረ​ገ​ሎ​ቹ​ንም፥ ሕዝ​ቡ​ንም ሁሉ ወደ አንተ ወደ ቂሶን ወንዝ እስ​ባ​ለሁ፤ በእ​ጅ​ህም አሳ​ልፌ እሰ​ጠ​ዋ​ለሁ።”


ነገ​ሥ​ታት መጡ፤ ተዋ​ጉም፤ በዚያ ጊዜ በመ​ጌዶ ውኆች አጠ​ገብ በቶ​ናሕ የከ​ነ​ዓን ነገ​ሥ​ታት ተዋጉ፤ በቅ​ሚ​ያም ብርን አል​ወ​ሰ​ዱም።