የብንያምም ልጆች የእስራኤል ልጆች ወደ መሴፋ እንደ ወጡ ሰሙ። የእስራኤልም ልጆች፥ “ይህ ክፉ ነገር እንደምን እንደ ተደረገ ንገሩን” አሉ።
መሳፍንት 20:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የተገደለችውም ሴት ባል ሌዋዊዉ እንዲህ ብሎ መለሰላቸው፥ “እኔና ዕቅብቴ በዚያ ለማደር ወደ ብንያም ሀገር ወደ ገባዖን መጣን። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ የተገደለችው ሴት ባል ሌዋዊ እንዲህ ሲል መለሰ፤ “እኔና ቁባቴ በዚያ ለማደር በብንያም ወደምትገኘው ወደ ጊብዓ መጣን። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህ የተገደለችው ሴት ባል ሌዋዊ እንዲህ ሲል መለሰ፤ “እኔና አባቴ በዚያ ለማደር በብንያም ወደምትገኘው ወደ ጊብዓ መጣን። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ቊባቱ የተገደለችበት ያ ሌዋዊ እንዲህ ሲል መለሰ፤ “እኔና ቊባቴ ሌሊቱን ለማሳለፍ በብንያም ግዛት ወደምትገኘው ወደ ጊብዓ ሄድን፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የተገደለችውም ሴት ባል ሌዋዊው እንዲህ ብሎ መለሰላቸው፦ እኔና ቁባቴ በዚያ ለማደር ወደ ብንያም አገር ወደ ጊብዓ መጣን። |
የብንያምም ልጆች የእስራኤል ልጆች ወደ መሴፋ እንደ ወጡ ሰሙ። የእስራኤልም ልጆች፥ “ይህ ክፉ ነገር እንደምን እንደ ተደረገ ንገሩን” አሉ።
የገባዖንም ሰዎች ተነሡብን፤ ቤቱንም በሌሊት በእኛ ላይ ከበቡት፤ ሊገድሉኝም ወደዱ፤ ዕቅብቴንም አዋረድዋት፤ አመነዘሩባትም፤ እርስዋም ሞተች።