እግዚአብሔርም ለሶርያውያን የሰረገላ ድምፅ፥ የፈረስ ድምፅና የብዙ ጭፍራ ድምፅ አሰምቶአቸዋልና፥ እርስ በርሳቸው “እነሆ፥ የእስራኤል ንጉሥ ይከቡን ዘንድ የኬጤዎናውያንንና የግብፃውያንን ነገሥት ቀጥሮ አምጥቶብናል” ይባባሉ ነበር።
መሳፍንት 1:26 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሰውየውም ወደ ኬጤዎናውያን ምድር ሄደ፤ በዚያም ከተማን ሠራ፤ ስምዋንም ሎዛ ብሎ ጠራት። እስከ ዛሬም ድረስ ስምዋ ያው ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሰውየውም ወደ ኬጢያውያን ምድር ሄዶ ከተማ ሠራ፤ ስሟንም ሎዛ ብሎ ጠራት፤ እስከ ዛሬም የምትጠራው በዚሁ ስም ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሰውየውም ወደ ኬጢያውያን ምድር ሄዶ ከተማ ሠራ፤ ስሟንም ሎዛ ብሎ ጠራት፤ እስከ ዛሬም የምትጠራው በዚሁ ስም ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ያም ሰው ዘግይቶ ወደ ሒታውያን ምድር ሄዶ ከተማ ሠራና “ሎዛ” ብሎ ሰየማት፤ እስከ ዛሬም የምትጠራበት ስም ይኸው ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሰውየውም ወደ ኬጢያውያን ምድር ሄደ፥ በዚያም ከተማን ሠራ፥ ስምዋንም ሎዛ ብሎ ጠራት። እስከ ዛሬም ድረስ ስምዋ ይህ ነው። |
እግዚአብሔርም ለሶርያውያን የሰረገላ ድምፅ፥ የፈረስ ድምፅና የብዙ ጭፍራ ድምፅ አሰምቶአቸዋልና፥ እርስ በርሳቸው “እነሆ፥ የእስራኤል ንጉሥ ይከቡን ዘንድ የኬጤዎናውያንንና የግብፃውያንን ነገሥት ቀጥሮ አምጥቶብናል” ይባባሉ ነበር።
ሄደውም ከግብፅ አንድ ሰረገላ በስድስት መቶ ብር፥ አንድንም ፈረስ በመቶ አምሳ ሰቅል ብር አመጡ፤ እንዲሁም ለኬጢያውያንና ለሦርያ ነገሥታት ሁሉ በየተራቸው ያመጡላቸው ነበር።
ምናሴም የሰቂቶን ከተማ ቤትሶንንና መንደሮችዋን መሰማሪያዎችዋንም፥ ኢቀጸአድንና መንደሮችዋን፥ የዶርን ነዋሪዎችና መንደሮችዋን፥ የዮበለዓምን ነዋሪዎች፥ መሰማሪያዎችዋንና መንደሮችዋን፥ የመጊዶን ነዋሪዎች መሰማሪያዎችዋንና መንደሮችዋን አልወረሳቸውም፤ ነገር ግን ከነዓናውያን በዚያች ሀገር ይቀመጡ ዘንድ ጸኑ።