ኢያሱ 11:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በእነዚያም ወራት ኢያሱ ተመልሶ አሶርን ያዘ፤ ንጉሥዋንም በሰይፍ ገደለ፤ አሶርም አስቀድሞ የእነዚህ መንግሥታት ዋና ከተማ ነበረች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚያ ጊዜም ኢያሱ ወደ ኋላ ተመልሶ አሦርን ያዘ፤ ንጉሧንም በሰይፍ ገደለው፤ አሦርም ቀድሞ በእነዚህ ሁሉ መንግሥታት ላይ የበላይነት ነበራት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚያን ጊዜም ኢያሱ ተመልሶ አሦርን ያዘ፥ ንጉሥዋንም በሰይፍ ገደለ፤ አሦርም አስቀድሞ የእነዚህ መንግሥታት ዋና ከተማ ነበረች። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኢያሱም ወደ ኋላ ተመልሶ ሐጾርን ድል ነሥቶ ያዘ፤ ንጉሥዋንም በሰይፍ ገደለ፤ ሐጾር በዚያን ዘመን ከነበሩት የዘውድ መንግሥታት ሁሉ የሚበልጥ ኀይል ያላት ነበረች። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዚያን ጊዜም ኢያሱ ተመልሶ አሶርን ያዘ፥ ንጉሥዋንም በሰይፍ ገደለ፥ አሶርም አስቀድሞ የእነዚህ መንግሥታት ዋና ከተማ ነበረች። |
እግዚአብሔርም በአሦር በነገሠው በከነዓን ንጉሥ በኢያቢን እጅ አሳልፎ ሰጣቸው፤ የሠራዊቱም አለቃ ሲሣራ ነበረ፤ እርሱም በአሕዛብ አሪሶት ይቀመጥ ነበረ።