La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዮሐንስ 6:65 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እን​ዲ​ህም አላ​ቸው፥ “ስለ​ዚህ እላ​ች​ኋ​ለሁ፤ ከአብ ካል​ተ​ሰ​ጠው በቀር ወደ እኔ መም​ጣት የሚ​ቻ​ለው የለም።”

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ቀጥሎም፣ “ ‘ከአብ ካልተሰጠው በቀር፣ ማንም ወደ እኔ ሊመጣ አይችልም’ ያልኋችሁ ለዚህ ነው” አለ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

እንዲህም አለ፦ “ስለዚህ አልኋችሁ፤ ከአብ የተሰጠው ካልሆነ ወደ እኔ ሊመጣ የሚችል የለም፥ ያልኋችሁ በዚህ ምክንያት ነው።”

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ቀጥሎም ኢየሱስ “ከአብ የተፈቀደለት ካልሆነ በቀር ወደ እኔ መምጣት የሚችል የለም ያልኳችሁ ስለዚህ ነው” አለ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ደግሞ፦ ስለዚህ አልኋችሁ፥ ከአብ የተሰጠው ካልሆነ ወደ እኔ ሊመጣ የሚችል የለም አለ።

Ver Capítulo



ዮሐንስ 6:65
14 Referencias Cruzadas  

እርሱም መልሶ እንዲህ አላቸ “ለእናንተ የመንግሥተ ሰማያትን ምሥጢር ማወቅ ተሰጥቶአችኋል፤ ለእነርሱ ግን አልተሰጣቸውም።


ከዚህ ቦታ ያይ​ደሉ ሌሎች በጎ​ችም አሉኝ፤ እነ​ር​ሱ​ንም ወደ​ዚህ አመ​ጣ​ቸው ዘንድ ይገ​ባ​ኛል፤ ቃሌ​ንም ይሰ​ሙ​ኛል፤ ለአ​ንድ እረ​ኛም አንድ መንጋ ይሆ​ናሉ።


ዮሐ​ን​ስም መልሶ እን​ዲህ አለ፥ “ሰው ከሰ​ማይ ካል​ተ​ሰ​ጠው በስ​ተ​ቀር እርሱ ራሱ ጸጋን ገን​ዘብ ሊያ​ደ​ርግ ምንም አይ​ች​ልም።


አብ የሚ​ሰ​ጠኝ ሁሉ ወደ እኔ ይመ​ጣል፤ ወደ እኔ የሚ​መ​ጣ​ው​ንም ከቶ ወደ ውጭ አላ​ወ​ጣ​ውም።


ይህ​ንም ጸጋ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰጥ​ቶ​አ​ች​ኋል፤ ነገር ግን ስለ እርሱ መከራ ልት​ቀ​በ​ሉም ነው እንጂ ልታ​ም​ኑ​በት ብቻ አይ​ደ​ለም።


የጌታችንም ጸጋ በክርስቶስ ኢየሱስ ካሉ ከእምነትና ከፍቅር ጋር አብልጦ በዛ።


ደግሞም “ምናልባት እግዚአብሔር እውነትን ያውቁ ዘንድ ንስሓን ይሰጣቸዋልና ፈቃዱን ለማድረግ በዲያብሎስ ሕያዋን ሆነው ከተያዙበት ወጥመድ ወጥተው ወደ አእምሮ ይመለሳሉ፤” ብሎ የሚቃወሙትን በየዋህነት ይቅጣ።


የእ​ም​ነ​ታ​ች​ን​ንም ራስና ፈጻ​ሚ​ውን ኢየ​ሱ​ስን እን​ከ​ተ​ለው፤ እርሱ ነው​ርን ንቆ፥ በፊ​ቱም ስላ​ለው ደስታ በመ​ስ​ቀል ታግሦ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዙፋን ቀኝ ተቀ​ም​ጦ​አ​ልና።