ዮሐንስ 6:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጌታችን ኢየሱስም ዐይኖቹን አንሥቶ ብዙ ሰዎች ወደ እርሱ ሲመጡ አየና ፊልጶስን፥ “ለእነዚህ ሰዎች የምናበላቸው እንጀራ ከወዴት እንግዛ?” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኢየሱስም ቀና ብሎ ሲመለከት፣ ብዙ ሕዝብ ወደ እርሱ ሲመጣ አየ፤ ፊልጶስንም፣ “እነዚህ ሰዎች እንዲበሉ እንጀራ ከየት እንግዛ?” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኢየሱስም ዐይኖቹን አንሥቶ ብዙ ሕዝብ ወደ እርሱ ሲመጣ አየና ፊልጶስን “እነዚህ እንዲበሉ እንጀራ ከወዴት እንገዛለን?” አለው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚያን ጊዜ ኢየሱስ ብዙ ሕዝብ ወደ እርሱ ሲመጣ ቀና ብሎ አየና ፊልጶስን፦ “ለዚህ ሁሉ ሰው የሚበቃ ምግብ ከየት መግዛት እንችላለን?” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኢየሱስም ዓይኖቹን አንሥቶ ብዙ ሕዝብ ወደ እርሱ ሲመጣ አየና ፊልጶስን፦ እነዚህ እንዲበሉ እንጀራ ከወዴት እንገዛለን? አለው። |
ሐዋርያትም በተመለሱ ጊዜ ያደረጉትን ሁሉ ነገሩት፤ እርሱም ለብቻቸው ይዞአቸው ቤተ ሳይዳ ከምትባል ከተማ አጠገብ ወደ አለ ምድረ በዳ ወጡ።
እርሱም ወደ ጌታችን ወደ ኢየሱስ ወሰደው፤ ጌታችን ኢየሱስም ባየው ጊዜ፥ “ አንተ የዮና ልጅ ስምዖን ነህን? አንተ ኬፋ ትባላለህ፤” አለው፤ ትርጓሜውም ጴጥሮስ ማለት ነው።
ፊልጶስም ናትናኤልን አገኘውና፥ “ሙሴ በኦሪት፥ ነቢያትም ስለ እርሱ የጻፉለትን የዮሴፍን ልጅ የናዝሬቱን ኢየሱስን አገኘነው” አለው።
ጌታችን ኢየሱስም ናትናኤልን ወደ እርሱ ሲመጣ ባየው ጊዜ ስለ እርሱ “እነሆ፥ በልቡ ተንኰል የሌለበት እውነተኛ እስራኤላዊ ይህ ነው” አለ።
እናንተ እስከ አራት ወር ድረስ መከር ይሆናል የምትሉ አይደለምን? እነሆ፥ እላችኋለሁ፤ ዐይናችሁን አንሡ፤ መከሩም ሊደርስ እንደ ገረጣ ምድሩን ተመልከቱ።