ዮሐንስ 4:29 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “የሠራሁትን ሁሉ የነገረኝን ሰው ታዩ ዘንድ ኑ፤ እንጃ፥ እርሱ ክርስቶስ ይሆን?” አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ያደረግሁትን ሁሉ የነገረኝን ሰው ኑና እዩ፤ እርሱ ክርስቶስ ይሆን እንዴ?” አለች፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ያደረግሁትን ሁሉ የነገረኝን ሰው ኑና እዩ፤ እንጃ እርሱ ክርስቶስ ይሆንን?” አለች። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “የሠራሁትን ሁሉ የነገረኝን ሰው ኑ እዩ! ምናልባት እርሱ መሲሕ ይሆንን?” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ያደረግሁትን ሁሉ የነገረኝን ሰው ኑና እዩ፤ እንጃ እርሱ ክርስቶስ ይሆንን? አለች። |
እነሆ፥ እርሱ በገሀድ ይናገራል፤ እነርሱ ግን ምንም የሚሉት የለም፤ ይህ በእውነት ክርስቶስ እንደ ሆነ ምናልባት አለቆች ዐውቀው ይሆን?
ከሕዝቡም ብዙዎች አመኑበትና፥ “በውኑ ክርስቶስ በሚመጣበት ጊዜ ይህ ሰው ካደረገው ተአምራት የሚበልጥ ያደርጋልን?” አሉ።
ሳሙኤልም መልሶ ሳኦልን፥ “ባለ ራእዩ እኔ ነኝ፤ ዛሬም ከእኔ ጋር ወደ ባማ ኮረብታ በፊቴ ውጣና ምሳ ብላ፤ ነገም በጥዋት አሰናብትሃለሁ፤ በልብህም ያለውን ነገር ሁሉ እነግርሃለሁ፤