ዮሐንስ 21:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጌታችን ኢየሱስም፥ “አሁን ከያዛችኋቸው ዓሣዎች አምጡ” አላቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኢየሱስም፣ “አሁን ካጠመዳችሁት ዓሣ እስኪ አምጡ” አላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኢየሱስም “አሁን ካጠመዳችሁት ዓሣ አምጡ” አላቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኢየሱስም “አሁን ካጠመዳችሁት ዓሣ አምጡ” አላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኢየሱስም፦ “አሁን ካጠመዳችሁት ዓሣ አምጡ” አላቸው። |
ስምዖን ጴጥሮስም ወደ ታንኳ ገብቶ መቶ አምሳ ሦስት ታላላቅ ዓሣዎችን መልቶ የነበረውን መረብ ወደ ምድር ሳበ፤ ብዛቱም ይህን ያህል ሲሆን መረቡ አልተቀደደም።
ጌታችን ኢየሱስም ያን እንጀራ ይዞ አመሰገነ፤ ቈርሶም ለደቀ መዛሙርቱ ሰጣቸው፤ ደቀ መዛሙርቱም ለተቀመጡት ሰዎች ሰጡአቸው፤ ከዓሣውም እንዲሁ የፈለጉትን ያህል ሰጡአቸው።