ዮሐንስ 2:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አሳዳሪውም ያን የወይን ጠጅ የሆነውን ውኃ ቀምሶ አደነቀ፤ ከወዴት እንደ መጣም አላወቀም፤ የቀዱት አሳላፊዎች ግን የወይን ጠጅ የሆነውን ያን ውኃ ያውቁ ነበር። ውኃዉን የሞሉ እነርሱ ነበሩና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የድግሱ ኀላፊም ወደ ወይን ጠጅ የተለወጠውን ውሃ ቀመሰ፤ ሆኖም ከየት እንደ መጣ አላወቀም፤ ውሃውን የቀዱት አገልጋዮች ግን ያውቁ ነበር። እርሱም ሙሽራውን ለብቻው ጠርቶ፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አሳዳሪውም የወይን ጠጅ የሆነውን ውሃ በቀመሰ ጊዜ ከወዴት እንደመጣ አላወቀም፤ ውሃውን የቀዱት አገልጋዮች ግን ያውቁ ነበር፤ አሳዳሪው ሙሽራውን ጠርቶ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የግብዣው ኀላፊ ወደ ወይን ጠጅ የተለወጠውን ውሃ በቀመሰ ጊዜ፥ ከየት እንደ መጣ አላወቀም፤ ውሃውን የቀዱት አገልጋዮች ግን ያውቁ ነበር፤ ስለዚህ የግብዣው ኀላፊ፥ ሙሽራውን ጠርቶ እንዲህ አለው፦ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አሳዳሪውም የወይን ጠጅ የሆነውን ውሃ በቀመሰ ጊዜ ከወዴት እንደ መጣ አላወቀም፤ ውኃውን የቀዱት አገልጋዮች ግን ያውቁ ነበር፤ አሳዳሪው ሙሽራውን ጠርቶ፦ |
ኢየሱስም እንዲህ አላቸው “ሚዜዎች ሙሽራው ከእነርሱ ጋር ሳለ ሊያዝኑ ይችላሉን? ነገር ግን ሙሽራው ከእነርሱ የሚወሰድበት ወራት ይመጣል፤ በዚያ ጊዜም ይጦማሉ።
ጌታችን ኢየሱስም ውኃውን የወይን ጠጅ ወደ አደረገበት የገሊላ ክፍል ወደምትሆን ወደ ቃና ዳግመኛ ሄደ። በቅፍርናሆም ልጁ የታመመበት የንጉሥ ወገን የሆነ አንድ ሰው ነበረ፤
ፈቃዱን ሊያደርግ የሚወድድ ግን ትምህርቴ ከእግዚአብሔር ዘንድ እንደ ሆነች፥ የምናገረውም ከራሴ እንዳይደለ እርሱ ያውቃል።