ኢዮብ 41:24 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በተፈጠረ ጊዜ መላእክቴ የሣቁበት፥ እንደ እርሱ ያለ በምድር ላይ ምንም የለም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ደረቱ እንደ ዐለት የጠጠረ፣ እንደ ወፍጮ ድንጋይም የጠነከረ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በስተ ኋላው ብሩህ መንገድን ያበራል፥ ቀላዩም ሽበት ይመስላል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ልቡ እንደ ድንጋይ ጠንካራ ነው፤ ጥንካሬውም እንደ ወፍጮ ድንጋይ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በስተ ኋላው ብሩህ መንገድን ያበራል፥ ቀላዩም ሽበት ይመስላል። |
አቤቱ! ዐይኖችህ ለሃይማኖት አይደሉምን? አንተ ቀሥፈሃቸዋል፤ ነገር ግን አላዘኑም፤ ቀጥቅጠሃቸውማል፤ ነገር ግን ተግሣጽን እንቢ አሉ፤ ፊታቸውን ከድንጋይ ይልቅ አጠንክረዋል፤ ይመለሱም ዘንድ እንቢ አሉ።
የሠራዊትም ጌታ እግዚአብሔር በቀደሙት ነቢያት እጅ በመንፈሱ የላከውን ሕጉንና ቃሉን እንዳይሰሙ ልባቸውን እንደ አልማዝ አጠነከሩ፣ ስለዚህ ከሠራዊት ጌታ ከእግዚአብሔር ዘንድ ታላቅ ቍጣ መጣ።