ኢዮብ 30:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በሸለቆው ፈረፈርና በምድር ጕድጓድ ውስጥ በዓለትም ዋሻ ውስጥ ይኖራሉ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዐለት መካከል በምድር ጕድጓድ፣ በደረቅ ሸለቆ ዋሻ ውስጥ ለመኖር ተገደዱ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በሸለቆ ጉድጓድ፥ በምድርና በድንጋይም ዋሻ ውስጥ ይኖራሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም መኖሪያቸውንም በየዋሻውና በየገደሉ ሥር በተቈፈሩ ጒድጓዶች ውስጥ ለማድረግ ተገደዱ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በሸለቆ ፈረፈርና በምድር ጕድጓድ በድንጋይም ዋሻ ውስጥ ይኖራሉ። |
እግዚአብሔርም ምድርን ያናውጥ ዘንድ በተነሣ ጊዜ እግዚአብሔርን ከመፍራትና ከግርማው ክብር የተነሣ ወደ ድንጋይ ዋሻና ወደ ምድር ንቃቃት ውስጥ ያገቡአቸዋል።
የምድያምም እጅ በእስራኤል ላይ ጠነከረች፤ ከምድያምም ፊት የተነሣ የእስራኤል ልጆች በተራሮችና በገደሎች ላይ ጕድጓድና ዋሻ፥ ምሽግም አበጁ።