La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ኢሳይያስ 42:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

አይ​ጮ​ኽም፤ ቃሉ​ንም አያ​ነ​ሣም፤ ድም​ፁ​ንም በሜዳ አያ​ሰ​ማም።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

አይጮኽም፣ ቃሉን ከፍ አያደርግም፤ ድምፁን በመንገድ ላይ በኀይል አያሰማም።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

አይጮኽም ቃሉንም አያነሣም፥ ድምፁንም በሜዳ አያሰማም።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ጮኾ አይናገርም፤ ድምጡንም በየአደባባዩ እንዲሰማ አያደርግም።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

አይጮኽም ቃሉንም አያነሣም፥ ድምፁንም በሜዳ አያሰማም።

Ver Capítulo



ኢሳይያስ 42:2
8 Referencias Cruzadas  

እነሆ፥ ደግፌ የያ​ዝ​ሁት ባሪ​ያዬ ያዕ​ቆብ፤ ነፍሴ የተ​ቀ​በ​ለ​ችው ምርጤ እስ​ራ​ኤ​ልም፤ በእ​ርሱ ላይ መን​ፈ​ሴን አድ​ር​ጌ​አ​ለሁ፤ እር​ሱም ለአ​ሕ​ዛብ ፍር​ድን ያመ​ጣል።


የተ​ቀ​ጠ​ቀጠ ሸን​በ​ቆን አይ​ሰ​ብ​ርም፤ የሚ​ጤ​ስ​ንም ክር አያ​ጠ​ፋም፤ ነገር ግን በእ​ው​ነት ፍር​ድን ያመ​ጣል።


አንቺ የጽዮን ልጅ ሆይ፥ እጅግ ደስ ይበልሽ፣ አንቺ የኢየሩሳሌም ልጅ ሆይ፥ እልል በዪ፣ እነሆ፥ ንጉሥሽ ጻድቅና አዳኝ ነው፣ ትሑትም ሆኖ በአህያም፥ በአህያይቱ ግልገል በውርጫንይቱ ላይ ተቀምጦ ወደ አንቺ ይመጣል።


ቀንበሬን በላያችሁ ተሸከሙ፤ ከእኔም ተማሩ፤ እኔ የዋህ በልቤም ትሑት ነኝና፤ ለነፍሳችሁም ዕረፍት ታገኛላችሁ፤


ፈሪ​ሳ​ው​ያ​ንም “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ግ​ሥት መቼ ትመ​ጣ​ለች?” ብለው ጠየ​ቁት፤ እር​ሱም መልሶ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ግ​ሥት በመ​ጠ​ባ​በቅ አት​መ​ጣም።


የጌታም ባሪያ ለሰው ሁሉ ገር፥ ለማስተማርም የሚበቃ፥ ለትዕግሥትም የሚጸና ሊሆን እንጂ ሊጣላ አይገባውም።


ሲሰድቡት መልሶ አልተሳደበም፤ መከራንም ሲቀበል አልዛተም፤ ነገር ግን በጽድቅ ለሚፈርደው ራሱን አሳልፎ ሰጠ፤