በመሸም ጊዜ ሳይነጋ ያለቅሳሉ፤ ያንጊዜም የይሁዳ ወገኖች “ይህ የወራሾች ርስት ነው፤ የበዘበዙንም ዕድል ፋንታ ይህ ነው” ይላሉ።
ኢሳይያስ 41:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሚያሠቃዩህንም ሰዎች ትሻቸዋለህ፤ አታገኛቸውምም፤ እንዳልነበሩ ይሆናሉና፤ የሚዋጋህም የለም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጠላቶችህን ብትፈልጋቸው እንኳ፣ አታገኛቸውም፤ የሚዋጉህም፣ እንዳልነበሩ ይሆናሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሚጣሉህንም ትፈልጋቸዋለህ አታገኛቸውምም፥ የሚዋጉህም እንዳልነበሩና እንደ ምናምን ይሆናሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጠላቶችህን ትፈልጋቸዋለህ፤ ነገር ግን አታገኛቸውም፤ በአንተ ላይ ጦርነት አስነሥተው የነበሩትም ፈጽሞ እንዳልነበሩ ይሆናሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሚያጣሉህንም ትሻቸዋለህ አታገኛቸውምም፥ የሚዋጉህም እንዳልነበሩና እንደ ምናምን ይሆናሉ። |
በመሸም ጊዜ ሳይነጋ ያለቅሳሉ፤ ያንጊዜም የይሁዳ ወገኖች “ይህ የወራሾች ርስት ነው፤ የበዘበዙንም ዕድል ፋንታ ይህ ነው” ይላሉ።
ሰዎች ተርበው ሌሊት በሕልማቸው ይበላሉ፤ ይጠጣሉም፤ በተነሡ ጊዜ ግን ሕልማቸው ከንቱ ነው። የተጠማ ሰውም እንደሚጠጣ ያልማል፤ በነቃም ጊዜ እንደ ተጠማ ነው፤ ነፍሱም በከንቱ ትመኛለች። ደብረ ጽዮንን የሚዋጉ የአሕዛብ ብልጽግናም እንደዚሁ ነው።
እግዚአብሔር ግን እንዲህ ይላል፥ “በኀያላን የተማረኩ ይወሰዳሉ፤ የጨካኞችም ብዝበዛ ያመልጣል፤ እኔም ፍርድሽን እፈርድልሻለሁ፤ ልጆችሽንም አድናለሁ።
በዚያ ዘመን እነሆ፥ ባስጨነቁሽ ሁሉ ላይ አደርግባቸዋለሁ፣ አንካሳይቱንም አድናለሁ፥ የተጣለችውንም እሰበስባታለሁ፣ ባፈሩባትም ምድር ሁሉ ላይ ለምስጋናና ለከበረ ስም አደርጋቸዋለሁ።