ሕዝቡም ወጥቶ የሶርያውያንን ሰፈር በዘበዘ፤ እንደ እግዚአብሔርም ቃል አንድ መስፈሪያ መልካም ዱቄት በአንድ ሰቅል፥ ሁለት መስፈሪያ ገብስም በአንድ ሰቅል ተሸመተ።
ኢሳይያስ 33:23 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ገመዶችሽ ተበጥሰዋል፤ ጥንካሬ የላቸውምና፤ ደቀልሽ ዘመመ፤ ሸራውንም መዘርጋት አልቻለም፤ እስከሚያዝም ድረስ አላማውን አልተሸከመም። በዚያን ጊዜ የብዙ ምርኮ ተከፈለ፤ ብዙ አንካሶች እንኳ ምርኮውን ማረኩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም መወጠሪያ ገመድህ ላልቷል፤ ምሰሶው ጠብቆ አልተተከለም፤ ሸራው አልተወጠረም፤ በዚያ ጊዜ ታላቅ ምርኮ ይከፋፈላል፤ ዐንካሳ እንኳ ሳይቀር ምርኮ ይወስዳል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ገመዶችህ ላልተዋል፥ ችካላቸውንም አልጸናም፥ ሸራውንም መወጠር አልቻሉም። በዚያን ጊዜ የብዙ ምርኮ ሀብት ይከፋፈላል፤ አንካሶች እንኳ ከክፍፍሉ ይደርሳቸዋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሕዝባችሁ ግን የምሰሶው ገመድ እንደ ላላ ምሰሶውም እንዳልጸና፥ ሸራውም እንዳልተዘረጋ መርከብ ነው፤ ከዚያ በኋላ የተትረፈረፈ ምርኮ ይከፋፈላል፤ አንካሶች እንኳ ገብተው ይበዘብዛሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ገመዶችህ ላልተዋል፥ ደቀላቸውንም አላጸኑም፥ ሸራውንም መዘርጋት አልቻሉም። በዚያን ጊዜ የብዙ ምርኮ ብዝበዛ ተከፈለ፥ አንካሶች እንኳ ብዝበዛውን በዘበዙ። |
ሕዝቡም ወጥቶ የሶርያውያንን ሰፈር በዘበዘ፤ እንደ እግዚአብሔርም ቃል አንድ መስፈሪያ መልካም ዱቄት በአንድ ሰቅል፥ ሁለት መስፈሪያ ገብስም በአንድ ሰቅል ተሸመተ።
እነዚያም ለምጻሞች ወደ ሰፈሩ መጀመሪያ ዳርቻ በመጡ ጊዜ ወደ አንድ ድንኳን ገብተው በሉ፤ ጠጡም፤ ከዚያም ወርቅና ብር ልብስም ወሰዱ፤ ሄደውም ሸሸጉት፤ ተመልሰውም ወደ ሌላ ድንኳን ገቡ፤ ከዚያም ደግሞ ወስደው ሸሸጉ።
ኢዮሳፍጥና ሕዝቡም ምርኮ ይወስዱ ዘንድ መጡ፤ ብዙ ከብትና ልዩ ልዩ ዕቃም፥ ልብስም፥ እጅግም ያማረ ዕቃ አገኙ፤ ማረኩትም፤ ምርኮውም ብዙ ነበርና ምርኮውን እየሰበሰቡ እስከ ሦስት ቀን ድረስ ቈዩ።
እኔስ በጸሎቴ ወደ እግዚአብሔር ነኝ የእግዚአብሔር ይቅርታው በጊዜው ነው፤ ይቅርታህ ብዙ ሲሆን መድኃኒቴ ሆይ፥ በእውነት አድነኝ።
ለሚያዋርዱአችሁ ወዮላቸው! እናንተን ግን የሚያዋርዳችሁ የለም፤ የሚወነጅላችሁ እናንተን የሚወነጅል አይደለም፤ ወንጀለኞች ይጠመዳሉ፤ ይያዛሉም፤ ብል እንደበላው ልብስም ያልቃሉ።
የእግዚአብሔር ስም ለእናንተ ታላቅ ነው፤ ሀገራችሁም የሰፉ ወንዞችና ታላቅ የመስኖ ስፍራ ይሆናል፤ በዚህች መንገድ አትሄድም፤ መርከቦችም አይሄዱም።
በዚያን ጊዜ አንካሳዎች እንደ ሚዳቋ ይዘልላሉ፤ የዲዳዎችም ምላስ ርቱዕ ይሆናል፤ በምድረ በዳ ውኃ፥ በተጠማ መሬትም ፈሳሽ ይፈልቃልና።
ሳባና ድዳን፥ የተርሴስም ነጋዴዎች፥ መንደሮችዋም ሁሉ፦ ምርኮን ትማርክ ዘንድ መጥተሃልን? ብዝበዛንስ ትበዘብዝ ዘንድ፥ ብርንና ወርቅንስ ትወስድ ዘንድ፥ ከብትንና ዕቃንስ ትወስድ ዘንድ፥ እጅግስ ብዙ ምርኮ ትማርክ ዘንድ ወገንህን ሰብስበሃልን? ይሉሃል።”
ነገር ግን እግዚአብሔር ጥበበኞችን ሊያሳፍር የዚህን ዓለም ሰነፎች መረጠ፤ ኀይለኞችንም ያሳፍር ዘንድ እግዚአብሔር የዚህን ዓለም ደካሞች መረጠ።
ዳዊትም ከእርሱም ጋር ያሉት አራት መቶ ሰዎች አሳደዱ፤ ሁለቱ መቶ ሰዎች ግን የቦሦር ወንዝን መሻገር ደክመዋልና በኋላ ቀሩ።