ዘፍጥረት 9:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከመርከብ የወጡት የኖኅ ልጆችም እነዚህ ናቸው፤ ሴም፥ ካም፥ ያፌት፤ ካምም የከነዓን አባት ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከመርከቧ የወጡትም የኖኅ ልጆች ሴም፣ ካምና ያፌት ነበሩ፤ ካም የከነዓን አባት ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከመርከቡ የወጡት የኖኅ ልጆች ሴም፥ ካምና ያፌት ናቸው፤ ካም የከነዓን አባት ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከመርከቡ የወጡት የኖኅ ልጆች ሴም፥ ካምና ያፌት ናቸው፤ ካም የከነዓን አባት ነው፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከመርከብ የወጡት የኖኅ ልጆችም እነዚህ ናቸው፤ ሴም፥ ካም፥ ያፌት፤ ካምም የከነዓን አባት ነው። |
እግዚአብሔርም ኖኅን፥ “በእኔና በምድር ላይ በሚኖር፥ ሥጋ ባለው ሁሉ መካከል ያጸናሁት የቃል ኪዳን ምልክት ይህ ነው” አለው።
ሴምና ያፌትም ልብስ ወስደው በጫንቃቸው ላይ አደረጉ፤ የኋሊትም ሄደው የአባታቸውን ዕራቁትነት አለበሱ፤ ፊታቸውም ወደ ኋላ ነበር፤ የአባታቸውንም ዕራቁትነት አላዩም።