ከምድርም ላይ ውኃዉ ጐድሎ እንደሆነ ያይ ዘንድ ቁራውን ላከው፤ እርሱም ሄደ፤ ነገር ግን ውኃው ከምድር ላይ እስኪደርቅ ድረስ አልተመለሰም።
ዘፍጥረት 8:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ርግብንም ውኃው ከምድር ፊት ጐድሎ እንደ ሆነ እንድታይ ከእርሱ በኋላ ላካት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም በኋላ፣ ኖኅ ውሃው ከምድር ገጽ ጐድሎ እንደ ሆነ ለማወቅ ርግብን ላከ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚህ በኋላ ኖኅ ውሃው ከምድር ላይ መጉደሉን ለማወቅ አንዲት ርግብ ላከ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ ኖኅ ውሃው ከምድር ላይ መጒደሉን ለማወቅ አንዲት ርግብ ላከ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ርግብንም ውኃው ከምድር ፊት ቀልሎ እንደ ሆነ እንድታይ ከእርሱ ዘንድ ሰደዳት። |
ከምድርም ላይ ውኃዉ ጐድሎ እንደሆነ ያይ ዘንድ ቁራውን ላከው፤ እርሱም ሄደ፤ ነገር ግን ውኃው ከምድር ላይ እስኪደርቅ ድረስ አልተመለሰም።
ነገር ግን ርግብ እግርዋን የምታሳርፍበት ስፍራ አላገኘችም፤ ወደ እርሱም ወደ መርከብ ተመለሰች፤ ውኃው በምድር ላይ ሁሉ ነበረና፤ እጁን ዘረጋና ተቀበላት፤ ወደ እርሱም ወደ መርከብ ውስጥ አገባት።