ላሜሕም ኖኅን ከወለደ በኋላ አምስት መቶ ስድሳ አምስት ዓመት ኖረ፤ ወንዶችንም ሴቶችንም ወለደ።
ላሜሕ ኖኅን ከወለደ በኋላ፣ 595 ዓመት ኖረ፤ ሌሎች ወንዶችና ሴቶች ልጆችንም ወለደ።
ኖኅንም ከወለደ በኋላ ላሜሕ አምስት መቶ ዘጠና አምስት ዓመት ኖረ፥ ሌሎች ወንድ እና ሴት ልጆችም ወለደ።
ከዚህ በኋላ ላሜክ 595 ዓመት ኖረ፤ ሌሎችንም ወንዶችና ሴቶች ልጆች ወለደ፤
ላሜሕም ኖኅን ከወለደ በኍላ የኖረው አምስት መቶ ስድሳ አምስት ዓመት ሆነ ወንዶችንም ሴቶችንም ወለደ።
ስሙንም ከሥራዬ፥ ከእጄ ድካምና እግዚአብሔር ከረገማት ምድር ይህ ያሳርፈኝ ዘንድ አለው ሲል “ኖኅ” ብሎ ጠራው።
ላሜሕም የኖረበት ዘመን ሁሉ ሰባት መቶ አርባ ሰባት ዓመት ሆነ፤ ሞተም።
አዳምም ሴትን ከወለደ በኋላ የኖረው ሰባት መቶ ዓመት ሆነ፤ ወንዶችንም፥ ሴቶችንም ወለደ።