ይህንም ነገር በየዕለቱ ለዮሴፍ ትነግረው ነበር፤ እርሱም ከእርስዋ ጋር ይተኛ ዘንድ፥ ከእርስዋም ጋር ይሆን ዘንድ አልሰማትም።
ዘፍጥረት 39:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ልብሱን ይዛ፥ “ና ከእኔ ጋር ተኛ” አለችው፤ እርሱም ልብሱን በእጅዋ ትቶላት ሸሸ፤ ወደ ውጭም ወጣ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሷም ልብሱን ጨምድዳ ይዛ “በል ዐብረኸኝ ተኛ” አለችው። እርሱ ግን ልብሱን እጇ ላይ ጥሎ ሸሽቶ ከቤት ወጣ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሷም ልብሱን ጨምድዳ ይዛ “በል አብረኸኝ ተኛ” አለችው። እርሱ ግን ልብሱን እጇ ላይ ጥሎ ሸሽቶ ከቤት ወጣ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚያን ጊዜ የጌታው ሚስት ልብሱን ይዛ “ከእኔ ጋር ተኛ” አለችው፤ እርሱ ግን ልብሱን እጅዋ ላይ ትቶላት ከቤት ሸሽቶ ወጣ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከእኔ ጋር ተኛ ስትል ልብሱን ተጠማጥማ ያዘች እርሱም ልብሱን በእጅዋ ትቶላት ሸሸ ወደ ውጭም ወጣ። |
ይህንም ነገር በየዕለቱ ለዮሴፍ ትነግረው ነበር፤ እርሱም ከእርስዋ ጋር ይተኛ ዘንድ፥ ከእርስዋም ጋር ይሆን ዘንድ አልሰማትም።
በአንዲትም ቀን እንዲህ ሆነ፤ በዚያ ቀን ሥራውን እንዲሠራ ዮሴፍ ወደ ቤቱ ገባ፤ በቤትም ውስጥ ከቤተ ሰዎች ማንም አልነበረም።
እርሱም እንቢ አለ፤ ለጌታውም ሚስት እንዲህ አላት፥ “እነሆ፥ ጌታዬ በቤቱ ያለውን ሁሉ ለእኔ በእጄ አስረክቦኛል፤ በቤቱ ያለውንም ምንም የሚያውቀው የለም፤
እኔም ከሞት ይልቅ የመረረች ነገርን አገኘሁ፤ እርስዋም ልብዋ ወጥመድና መረብ የሆነ፥ በእጆችዋም ማሰሪያ ያላት ሴት ናት፤ በእግዚአብሔርም ፊት ደግ የሆነ ከእርሷ ያመልጣል። ኀጢአተኛ ግን ይጠመድባታል።