Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘፍጥረት 39:12 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 እርሷም ልብሱን ጨምድዳ ይዛ “በል ዐብረኸኝ ተኛ” አለችው። እርሱ ግን ልብሱን እጇ ላይ ጥሎ ሸሽቶ ከቤት ወጣ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 እርሷም ልብሱን ጨምድዳ ይዛ “በል አብረኸኝ ተኛ” አለችው። እርሱ ግን ልብሱን እጇ ላይ ጥሎ ሸሽቶ ከቤት ወጣ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 በዚያን ጊዜ የጌታው ሚስት ልብሱን ይዛ “ከእኔ ጋር ተኛ” አለችው፤ እርሱ ግን ልብሱን እጅዋ ላይ ትቶላት ከቤት ሸሽቶ ወጣ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 ልብ​ሱን ይዛ፥ “ና ከእኔ ጋር ተኛ” አለ​ችው፤ እር​ሱም ልብ​ሱን በእ​ጅዋ ትቶ​ላት ሸሸ፤ ወደ ውጭም ወጣ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 ከእኔ ጋር ተኛ ስትል ልብሱን ተጠማጥማ ያዘች እርሱም ልብሱን በእጅዋ ትቶላት ሸሸ ወደ ውጭም ወጣ።

Ver Capítulo Copiar




ዘፍጥረት 39:12
16 Referencias Cruzadas  

ከወጣትነት ክፉ ምኞት ሽሽ፤ በንጹሕ ልብ ጌታን ከሚጠሩት ጋራም ጽድቅን፣ እምነትን፣ ፍቅርንና ሰላምን ተከታተል።


ወዳጆች ሆይ፤ በዚህ ዓለም እንግዶችና መጻተኞች እንደ መሆናችሁ መጠን፣ ነፍስን ከሚዋጋ ሥጋዊ ምኞት እንድትርቁ እለምናችኋለሁ።


ልቧ ወጥመድና አሽክላ፣ እጆቿም እግር ብረት የሆኑ፣ ከሞት የከፋችዋን ሴት አገኘሁ፤ አምላክን ደስ የሚያሰኝ ከእጇ ያመልጣል፤ ኀጢአተኛውን ግን አጥምዳ ትይዘዋለች።


ከዐዳኝ እጅ እንዳመለጠች ሚዳቋ፣ ከአጥማጅ ወጥመድ እንዳፈተለከች ወፍ ራስህን አድን።


መንገድህን ከርሷ አርቅ፤ በደጃፏም አትለፍ፤


አትሳቱ፤ “መጥፎ ጓደኛነት መልካሙን ጠባይ ያበላሻል።”


ምንም እንኳ ዮሴፍን በየቀኑ ብትጐተጕተውም፣ አልሰማትም፤ ከርሷ ጋራ መተኛት ይቅርና ዐብሯትም መሆን አልፈቀደም።


እርሱ ግን ፈቃደኛ አልሆነም፤ እንዲህም አላት፤ “ጌታዬ ያለውን ሁሉ በኀላፊነት ስለ ሰጠኝ፣ በቤቱ ውስጥ ስላለው ሁሉ ምንም የሚያውቀው ነገር የለም።


ልጄ ሆይ፤ ዐብረሃቸው አትሂድ፤ በሚሄዱበትም መንገድ እግርህን አታንሣ፤


ሳሙኤል ለመሄድ ዘወር ባለ ጊዜ፣ ሳኦል የልብሱን ጫፍ ያዘ፤ ተቀደደም።


አንድ ቀን ዮሴፍ የዕለት ተግባሩን ለማከናወን ወደ ቤት ገባ፤ ከቤቱ አገልጋዮችም አንድም ሰው በቤት ውስጥ አልነበረም።


እርሷም ልብሱን እጇ ላይ ጥሎ ሸሽቶ መውጣቱን ባየች ጊዜ፣


ነገር ግን ምግቡን ስታቀርብለት አፈፍ አድርጎ ያዛትና፣ “እኅቴ ነዪ ዐብረን እንተኛ” አላት።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios