La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘፍጥረት 37:32 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ብዙ ኅብር ያለ​በ​ትን ቀሚ​ሱ​ንም ላኩ፤ ወደ አባ​ታ​ቸ​ውም አገ​ቡት፤ እን​ዲ​ህም አሉት፥ “ይህን ልብስ አገ​ኘን፤ ይህ የል​ጅህ ልብስ እንደ ሆነ ወይም እን​ዳ​ል​ሆነ እስኪ እየው?”

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

በኅብረ ቀለማት ያጌጠችውን እጀ ጠባብ ወደ አባታቸው ወስደው፣ “ይህን ወድቆ አገኘነው፤ የልጅህ እጀ ጠባብ መሆን አለመሆኑን እስኪ እየው” አሉት።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ብዙ ኅብር ያለበትንም ልብሱን ወደ አባታቸው ወስደው “እነሆ፥ ይህን አገኘን የልጅህ ልብስ እንደሆነ ወይም እንዳልሆነ እይ” አሉት።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ብዙ ኅብር ያለበትንም ልብሱን ወደ አባታቸው ወስደው “እነሆ፥ ይህን አገኘን የልጅህ ልብስ እንደ ሆነ ወይም እንዳልሆነ እይ” አሉት።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ብዙ ኅብር ያለበት ቀሚሱንም ላኩ፥ ወደ አባታቸውም አገቡት እንዲህም አሉት፦ ይህንን አገኘነ ይህ የልጅህ ልብስ እንደ ሆነ ወይም እንዳልሆነ እስኪ እየው።

Ver Capítulo



ዘፍጥረት 37:32
7 Referencias Cruzadas  

ኑ፥ እን​ግ​ደ​ለ​ውና በአ​ንድ ጕድ​ጓድ ውስጥ እን​ጣ​ለው፤ ክፉ አው​ሬም በላው እን​ላ​ለን፤ ሕል​ሞ​ቹም ምን እን​ደ​ሚ​ሆኑ እና​ያ​ለን።”


ያዕ​ቆ​ብም ዮሴ​ፍን ከል​ጆቹ ሁሉ ይልቅ ይወ​ድ​ደው ነበር፤ እርሱ በሽ​ም​ግ​ል​ናው የወ​ለ​ደው ነበ​ርና። በብዙ ኅብር ያጌ​ጠ​ችም ቀሚስ አደ​ረ​ገ​ለት።


የዮ​ሴ​ፍ​ንም ቀሚስ ወሰዱ፤ የፍ​የ​ልም ጠቦት አር​ደው ቀሚ​ሱን በደም ነከ​ሩት።


እር​ሱም ዐውቆ፥ “የልጄ ቀሚስ ነው፤ ክፉ አውሬ በል​ቶ​ታል፤ ዮሴ​ፍን ቦጫ​ጭ​ቆ​ታል” አለ።


እር​ስ​ዋም ሲወ​ስ​ዱ​አት ወደ አማቷ እን​ዲህ ብላ ላከች፤ “ተመ​ል​ከት፦ ይህ ቀለ​በት፥ ይህ ኩፌት፥ ይህ በትር የማን ነው? ይህስ ፅንስ የማን ነው?”


ከአ​መ​ን​ዝ​ሮች ጋር ገን​ዘ​ብ​ህን ሁሉ የጨ​ረሰ ይህ ልጅህ በተ​መ​ለሰ ጊዜ ግን የሰ​ባ​ውን ፍሪዳ አረ​ድ​ህ​ለት።’