ዘፍጥረት 30:23 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወንድ ልጅንም ለያዕቆብ ወለደችና፥ “እግዚአብሔር ሽሙጤን ከእኔ አስወገደ” አለች፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ፀንሳ፣ ወንድ ልጅ ወለደችና “እግዚአብሔር ዕፍረቴን አስወገደልኝ” አለች፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ፀነሰችም፥ ወንድ ልጅንም ወለደችና፦ “እግዚአብሔር ስድቤን አስወገደ” አለች፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ፀንሳም ወንድ ልጅ ወለደች፤ “እግዚአብሔር ወንድ ልጅ ሰጠኝ፤ ስድቤንም አስወገደልኝ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ፀነሰችም፥ ወንድ ልጅንም ወለደችና፦ እግዚአብሔር ስድቤን አስወገደ አለች፤ |
በዚያም ቀን ሰባት ሴቶች፥ “የገዛ እንጀራችንን እንበላለን፤ የገዛ ልብሳችንንም እንለብሳለን፤ ስምህ ብቻ በእኛ ላይ ይጠራ፤ መሰደባችንንም አርቅልን” ብለው አንዱን ወንድ ይይዙታል።
አባቷንም፥ “ይህ ነገር ይደረግልኝ፤ ከዚህ ሄጄ በተራሮች ላይ እንድወጣና እንድወርድ፥ ከባልንጀሮቼም ጋር ለድንግልናዬ እንዳለቅስ ሁለት ወር አሰናብተኝ” አለችው።