La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘፍጥረት 18:24 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

አምሳ ጻድ​ቃን በከ​ተ​ማ​ዪቱ ውስጥ ቢገኙ በውኑ ሁሉን ታጠ​ፋ​ለ​ህን? ከተ​ማ​ዪ​ቱ​ንስ በእ​ር​ስዋ ስለ​ሚ​ገኙ አምሳ ጻድ​ቃን አት​ም​ር​ምን?

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ዐምሳ ጻድቃን በከተማዪቱ ቢገኙ፣ በውኑ ነዋሪዎቹን ሁሉ ታጠፋለህን? በውስጧ ለሚገኙ ዐምሳ ጻድቃን ስትል ከተማዪቱን ይቅር አትልምን?

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

አምሳ ጻድቃን በከተማይቱ ውስጥ ቢገኙ በውኑ ሁሉን ታጠፉለህን? ከተማይቱንስ በእርሷ ስለሚገኙ አምሳ ጻድቃን አትምርምን?

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

በከተማይቱ ውስጥ ኀምሳ ደጋግ ሰዎች ቢገኙ ከተማይቱን በሙሉ ትደመስሳለህን? ስለ ኀምሳው ደጋግ ሰዎች ስትል ከተማይቱ እንዳትጠፋ አታደርግምን?

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

አምሳ ጻድቃን በከተማይቱ ውስጥ ቢገኙ በውኑ ሁሉን ታጠፉለህብ? ከተማይቱንስ በእርስዋ ስለሚገኙ አምሳ ጻድቃን አትምርምን?

Ver Capítulo



ዘፍጥረት 18:24
8 Referencias Cruzadas  

አብ​ር​ሃ​ምም ቀረበ፤ አለም፥ “አቤቱ፥ ጻድ​ቃ​ንን ከኃ​ጥ​ኣን ጋር አታ​ጥፋ፤ ጻድቁ እንደ ኃጥኡ አይ​ሁን።


አቤቱ ይህ ለአ​ንተ አግ​ባብ አይ​ደ​ለም፤ ይህን ነገር አታ​ድ​ርግ፤ ጻድ​ቃ​ንን ከኃ​ጥ​ኣን ጋር አታ​ጥፋ፤ ምድ​ርን ሁሉ የም​ት​ገዛ ይህን ፍርድ ታደ​ርግ ዘንድ ለአ​ንተ አግ​ባብ አይ​ደ​ለም።”


አብ​ር​ሃ​ምም አለው፥ “አቤቱ እን​ደ​ገና እና​ገር ዘንድ ፍቀ​ድ​ልኝ፤ ከዚያ ዐሥር ቢገ​ኙሳ?” እር​ሱም፥ “ስለ ዐሥሩ አላ​ጠ​ፋ​ትም” አለው።


እንደ አንተ ያለ​ውን ሰው ክፋ​ትህ ይጎ​ዳ​ዋል፤ ለሰ​ውም ልጅ ጽድ​ቅህ ይጠ​ቅ​መ​ዋል።


የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘርን ባያ​ስ​ቀ​ር​ልን ኖሮ፥ እንደ ሰዶም በሆ​ንን፥ እንደ ገሞ​ራም በመ​ሰ​ልን ነበር።


“በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም መን​ገ​ዶች ሩጡ፤ ተመ​ል​ከ​ቱም፤ ዕወ​ቁም፤ በአ​ደ​ባ​ባ​ይ​ዋም ፈልጉ፤ ፍር​ድን የሚ​ያ​ደ​ር​ገ​ውን እው​ነ​ት​ንም የሚ​ሻ​ውን ሰው ታገኙ እንደ ሆነ ይቅር እላ​ቸ​ዋ​ለሁ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


እር​ሱም እን​ዲህ አለኝ፦ ‘ጳው​ሎስ ሆይ፥ አት​ፍራ፤ በቄ​ሣር ፊት ልት​ቆም ይገ​ባ​ሃል፤ ከአ​ን​ተም ጋር የሚ​ሄ​ዱ​ትን ሁሉ እነሆ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለአ​ንተ ሰጥ​ቶ​ሃል።’