ዘፍጥረት 14:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከኤላም ንጉሥ ከኮሎዶጎሞር፥ ከአሕዛብ ንጉሥ ከቴሮጋል፥ ከሰናዖር ንጉሥ ከአሜሮፌል፥ ከእላሳር ንጉሥ ከአርዮክ ጋር ተጋጠሙ። እነዚህ አራቱ ነገሥታት ከአምስቱ ነገሥታት ጋር ተዋጉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነዚህ ዐምስቱ፣ በኤላም ንጉሥ በኮሎዶጎምር፣ በጎይም ንጉሥ በቲድዓል፣ በሰናዖር ንጉሥ በአምራፌል፣ በእላሳር ንጉሥ በአርዮክ፣ በእነዚህ በአራቱ ላይ ዘመቱባቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የኤላምን ንጉሥ ኮሎዶጎምርን፥ የአሕዛብን ንጉሥ ቲድዓልን፥ የሰናዖርን ንጉሥ አምራፌልን፥ የእላሳርን ንጉሥ አርዮክን ለመውጋት አምስቱ ነገሥታት በእነዚህ በአራቱ ላይ ወጡ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የተዋጉትም ከዔላም፥ ከጎይም፥ ከባቢሎንና ከኤላሳር ነገሥታት ጋር ነበር፤ አምስቱ ነገሥታት ከአራቱ ነገሥታት ጋር የተዋጉት በዚህ ዐይነት ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የኤላምን ንጉሥ ኮሎዶጎምርን፤ የአሕዛብን ንጉሥ ቲድዓልን፤ የሰናዖርን ንጉሥ አምራፌልን፥ የእላሳርን ንጉሥ አርዮክን ለመውጋት አምስቱ ነገሥታት በእነዚህ በአራቱ ላይ ወጡ። |
በሰናዖር ንጉሥ በአሚሮፌል፥ በእላሳር ንጉሥ በአርዮክ፥ በኤላም ንጉሥ በኮሎዶጎሞር፥ በአሕዛብ ንጉሥ በቴሮጋል ዘመን እንዲህ ሆነ፤
ያም የጨው ሸለቆ የዝፍት ጕድጓዶች ነበሩበት። የሰዶም ንጉሥና የገሞራ ንጉሥም ሸሹና በዚያ ወደቁ፤ የቀሩትም ወደ ተራራማው ሀገር ሸሹ።
የሰዶም ንጉሥና የገሞራ ንጉሥ፥ የአዳማ ንጉሥና የሲባዮን ንጉሥ፥ ሴጎር የተባለች የባላቅ ንጉሥም ወጡ፤ እነዚህ ሁሉ በጨው ሸለቆ በእነርሱ ላይ ለሰልፍ ወጡ፤
በይሁዳ ንጉሥ በሴዴቅያስ በመጀመሪያው ዓመተ መንግሥት ስለ ኤላም ወደ ነቢዩ ወደ ኤርምያስ የመጣው የእግዚአብሔር ቃል ይህ ነው።