ዘፍጥረት 1:23 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ማታም ሆነ፤ ጥዋትም ሆነ፤ አምስተኛም ቀን ሆነ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም መሸ፤ ነጋም፤ ዐምስተኛ ቀን። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ማታም ሆነ ጥዋትም ሆነ፥ አምስተኛ ቀን። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ቀኑ መሸ፤ ሌሊቱም ነጋ፤ አምስተኛ ቀን ሆነ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ማታም ሆነ ጥዋትም ሆነ፤ አምስተኚ ቀን። |
እግዚአብሔርም አለ፥ “ምድር ሕያዋን ፍጥረታትን እንደ ወገኑ፥ እንስሳትንና ተንቀሳቃሾችን፥ የምድር አራዊትንም እንደየወገኑ ታውጣ፥” እንዲሁም ሆነ።
እግዚአብሔር ያን ጠፈር “ሰማይ” ብሎ ጠራው። እግዚአብሔርም ያ መልካም እንደሆነ አየ። ማታም ሆነ፤ ጥዋትም ሆነ፤ ሁለተኛም ቀን ሆነ።